ቀን 13/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ፣ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተሞች እውቅና ሰጠ።

በእውቅና መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ተሸላሚ ተማሪዎች ፣ ወላጆች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ተማሪዎቹ እንዳስመዘገቡት ውጤት ላፕቶፖችን ጨምሮ ታብሌት ሞባይል እንዲሁም ለውጤቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት የምስክር ወረቀት ከክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዕውቅና መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ የተመዘገበው ውጤት አበረታች ቢሆንም ከከተማው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ በመጠቆም የግል ጥረታቸውን ተጠቅመው ውጤታማ የሆኑ ተሸላሚ ተማሪዎች በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በብቃት አልፈው ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ዜጋ እንደሚሆኑ እምነታቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የዛሬው የዕውቅና መርሀ ግብር በነበራቸው ያልተቋረጠ ጥረት ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎችን በማበረታታት ሌሎች ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን እና መንፈሳዊ ቅናትን ለመፍጠር እንደሚረዳ ጠቁመው ለውጤቱ መምጣት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ መምህራን ወላጆችና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በ2014ዓ.ም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 20 ፐርሰንት ያህል ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ትምህርት ቤቶች መካከል 10ሩ አዲስ አበባ እንደሚገኙ በመጥቀስ ውጤቱ በቀጣይ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለተሻለ ውጤት የምንተጋበት ይሆናል በማለት አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s