ቀን 22 /7/2014 ዓ.ም

በእቴጌ መነን የልጃገረዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርተ ቤት ዓመታዊ የውስጥ ስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

በስፖርታዊ  ውድድሩ  የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ  በመገኘት  የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ  አካላትን  በማበረታታት ከቀለም ትምህርታቸዉ ጎን ለጉን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እራሳቸዉን እንዲያዳብሩ አደራ ብለዋል፡፡

 ስፖርታዊ ውድድሩ ለ ሁለት ወራት ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን  በእለቱ በተማሪዎች መካከል የእግር ካስ ፣ የቴካንዶ እና የሰርከስ ውድድሮች የተከናወኑ ሲሆን በመምህራን እና በአስተዳደር ሰራተኞች መካከል የገመድ ጉተታ ውድድር ተካሄዳል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/ ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 22 /7/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል  የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ፤ በተፋጠነ የትምህርት ትብብር  እና አጋርነት ስትራቴጂክ ማናል እና በሱፐርቪዥን አገልግሎት በተገኙ ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል  የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ግምገማ አፈጻጸም ላይ እንዲሁም የቀጣይ ሶስት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ  እንዲሁም   በተፋጠነ የትምህርት ትብብር  እና አጋርነት ስትራቴጂክ ማናል ላይ ገለጻ እና በሱፐርቪዥን አገልግሎት በተገኙ ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክጽል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ  እንዳስታወቁት የቀጣዩ ሶስት ዓመታት የትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል እቅድ ውጤታማ እንዲሆን  ያለፈዉን የትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል እቅድ አፈጻጸም በአግባቡ መገምገም ይገባል ብለዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም ስትራቴጂክ እቅዱ  እና ግምገማዉ  ተናባቢ ሊሆን እነደሚገባ አጽኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ከአዲስ ከተማ ፣ አቃቂ ቃሊቲ ፣ አራዳ  ፣ ቦሌ ፣ ጉለሌ እንዲሁም ቂርቆስ ክፍለከተሞች የሚገኙ የመንግስትና የግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና የክፍለከተሞቹ የሁለቱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ በነገው እለትም ከቀሪ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች ጋር ተመሳሳይ ውይይት እንደሚከናወን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 22 /7/2014 ዓ.ም

በማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ምልከታ ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እና የቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘዉ በማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት በመገኘት ምልከታ አካሂደዋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘዉ ማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑት ሚስተር ኢሳ ሴቨር ትምህርት ቤቱ  በቱርክ መንግስት በሚታገዘዉ ማሪፍ ፋውንዴሽን የሚተዳደር እንደሆነ በመግለጽ ፋውንዴሽኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 243 ትምህርት ቤቶችን እያስተዳደረ እንደሚገኝ አሳውቀዋል፡፡ ርዕሰ መምህሩ አክለዉም ትምህርት ቤቱ በትምህርት ዘርፍ ላይ የላቀ ድጋፍ ለመስጠት ከመንግስት ጎን ቆሞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አብይ ሀይሌ በበኩላቸዉ ማሪፍ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ከየካ ቅርንጫፍ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች በሲኤምሲ ፣ በአፍሪካ ህብረት ፣ በሳርቤት ፣ በሰበታ እና በሀረር እንዳሉት ገልፀዋል፡፡ አክለዉም ትምህርት ቤቱ  በኢትዮጵያ እና  በኢንተርናሽናል ሰርዓተ ትምህርት ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ  ገልፀዉ በየካ በሚገኘዉ ትምህርት ቤት 231 ተማሪዎች  ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ መሆናቸዉን አሳውቀዋል፡፡ አቶ አብይ  አክለዉም  ትምህርት ቤቱ ከጥቅምት  2014 ዓ.ም ጀምሮ ከኬጂ እሰከ 12ኛ ክፍል  ድረስ ማስተማር መጀመሩን በመግለጽ ተቋሙ ለተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል ማዘጋጀቱን አሳውቀዋል፡፡

ነጻ ትምህርት እድሉ በሚቀጥለዉ ዓመት 5ኛ ፣ 9ኛ እና 11ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች በቀረዉ አጭር የመመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ኦላይን በመመዝገብ የተዘጋጀዉን ፈተና ተፈትነዉ የሚጠበቀዉን ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 22/7/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ፎርም አሞላልና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከርዕሰ መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ እንዳስታወቁት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተማሪዎች ቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወሰንበት የትምህርት እርከን መሆኑን ጠቁመው ትምህርት ቤቶች የተፈታኝ ተማሪዎቻቸውን አጠቃላይ መረጃ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በከፍተኛ ጥንቃቄ በመመዝገብ ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ምዝገባ እና የምዝገባ ቅጽ አጠቃቆርን የተመለከተ መመሪያ ያቀረቡ ሲሆን በመመሪያውም የተማሪዎች መረጃ ፣ የትምህርት ቤቶችና የክፍለ ከተሞች ኮድ፤ የተመዝጋቢ ተማሪዎች መብትና ግዴታ የሚሉና ሌሎች መሰል ጉዳዮች መካተታቸውን አስታውቀዋል፡፡፡፡

በውይይቱ ከአዲስ ከተማ ፣ አቃቂ ቃሊቲ ፣ አራዳ  ፣ ቦሌ ፣ ጉለሌ እንዲሁም ቂርቆስ ክፍለከተሞች የሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና የክፍለከተሞቹ የሁለቱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ በነገው እለትም ከቀሪ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች ጋር ተመሳሳይ ውይይት እንደሚደረግ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 21/7/2014 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ ስር በሚገኘዉ መስከረም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በከተማ ግብርና በተሰራ ስራ የተገኘ ውጤት፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 21/7/2014 ዓ.ም

ስኮላርሺፕ

ቀን 20/7/2014 ዓ.ም

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት በስራ አሰራር ስርዓት እና በአመለካከት ለውጥ ላይ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

በውጤት አምጪ የስራ አሰራር ስርዓት እና በአመለካከት ለውጥ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ያስቻል ስልጠና ከትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ 165 የቡድን መሪዎች ፣ ባለሙያዎች ፣ሱፐርቫይዘሮች ፣ ርዕሳነ መምህራን እና መምህራን መስጠቱን የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌ ተናግረዋል፡፡

በውጤት አምጪ የስራ አሰራር ስርዓት እና በአመለካከት ለውጥ ዙሪያ ስልጠናው ያተኮረ እንደሆነ የጠቆሙት ሀላፊዋ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የተሻለ የስራ አሰራር ስርዓት ዘርግቶ ውጤታማ ከመሆን እና የተማሪዎቻችንን ውጤትና ስነ-ምግባር ከማሻሻል አኳያ ውስንነቶች በመታየታቸው ያንን ለመቅረፍም የተሰጠ ነው ብለዋል፡፡

ከአነዚህ ችግሮች በመውጣት አመለካከትን በማዘመን እና በውጤት አምጪ አሰራሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የትምህርት ስርዓቱ የሚፈልገውን ብቁ ዜጋ ማፍራት እና ለሀገር ልማት እድገት ሚናውን የሚወጣ ትውልድ ለመቅረፅ የሚደረገውን ጥረትንም ስልጠናዉ ይደግፋል ተብሏል፡፡

የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላትን የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ነው ያሉት ሀላፊዋ በዘርፉ ላይ የሚሰሩና በባለ ድርሻነት እየተሳተፉ ያሉ አካላት ጭምር በጋራ መስራት ወሳኝነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 19/7/2014 ዓ.ም

የእጅ ጥበቦች በትምህርት ቤት ውስጥ

አቶ መኩሪያ አመንቴ ይባላሉ በልደታ ክፍለ ከተማ በመዝገበ ብርሀን ት/ቤት ጥበቃና አትክልተኛ ናቸዉ ፡፡

አቶ መኩሪያ  በት/ቤቱ የእጅ ጥበቦችን በመስራት የት/ቤቱን ቅጥር ግቢ እያስዋቡና በሚሰሯቸው የእጅ ጥበቦች ተማሪዎች ሀገራቸውን እንዲያውቁ እያደረጉ ይገኛሉ።

ስራቸዉንም የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ ፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እና የከፍለ ከተማ አመራሮች በቦታው ተገኝተው አበረታተዋቸዋል።

አካባቢን በእጅ ጥበቦቸና አረንጓዴ በማድረግ ማስዋብ ደስታን ይሰጠኛል ያሉት አቶ መኩሪያ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ተቋማት ግቢና አደባባዮች ስራቸውን የማስፋት እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 2/7/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጅ ማህበር (ተወማ ) የ2014 ዓ.ም የ6 ወር አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

በግምገማው የክፍለ ከተማ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የተመረጡ ክፍለ ከተሞችና የከተማው የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አብይ ተፈራ እንዳስታወቁት የተማሪ ወላጅ ማህበሩ በከተማ አስተዳደሩ በመማር ማስተማር ስራው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ ውይይት ማህበሩ በየክፍለከተማውም ሆነ በከተማ ደረጃ ባከናወናቸው ተግባራት ላይ በመወያየት በቀጣይ ጊዜያት የተሻለ ስራ ለመስራት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጅ ማህበር ሰብሳቢ ኢንጅነር ጌታቸው ሰጠኝ በበኩላቸው ማህበሩ ባለፉት 6 ወራት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱንና በዚህም በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን መፍትሄ እንዲያገኙ መስራቱን ገልጸው ማህበሩ ማከናወን የሚጠበቅበትን ተግባር በሚጠበቅበት ልክ ተግባራዊ ለማድረግ ያለበት የበጀት ውስንነት ችግር እንደፈጠረበትም አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 1/7/2014 ዓ.ም

የትምህርት ቤት ምገባን ለማገዝ ከአንድ ማዕከል ግብዓቶችን ለማቅረብ እንዲቻል ስራ እየሰራ መሆኑን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አሳወቀ፡፡

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ለትምህርት ቤት መጋቢ እናቶች እፎይታን ለመፍጠር እንዲያግዝ እና ለሁሉም ት/ቤቶች ከአንድ ማእከል የእንጀራና የዳቦ አቅርቦት እንዲያገኙ የገበያ ትስስር እዲፈጠር ለማድረግ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በመሄድ የመስክ ምልከታ አድርጋል።

በመስክ ምልከታውም ላይ የክ/ከተማው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ ወርቁ እና በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ተሳተፊ ሆነዋል።

የመስክ ምልከታ የተደረገበት ማን እንደእናት የእንጀራና የዳቦ መጋገሪያ ድርጅት ባለቤት የሆኑት አቶ አልዓዛር አሰፋ ልዑኩን ባስጎበኙበት ወቅት የድርጅታቸዉን ዋና አላማ ሲገልጹ እንደ ዜጋ ለተማሪዎች  ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ  ዋጋ በሰዓቱ  ማቅረብ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ የድርጅቱ ባለቤት አክለዉም አንድ እንጀራ በ7ብር እና አንድ ዳቦ ተገቢውን ግራም የጠበቀ በ3 ብር የሚያስረክቡ መሆኑን ይህም ዋጋ ካለው ወቅታዊ  የገበያ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር  የተሻለ እንደሆነ ለሙከራም ወረዳ 4 ለሚገኘዉ  አራብሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በማቅረብ ውጤታማ በመሆናችን አሁን ላይ አቅርቦታችንን ለሁሉም ት/ቤቶች ለማስፋት አሰፈላጊውን ግብዓት ሟማላታቸዉን  ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዋንኛነት የኃይል መቆራረጥ እንዳይገጥማቸዉ የራሳችን ትራንስፎርመር እና ጄኔሬተር ያስገጠሙ መሆናቸዉን ፣ በቂ የዳቦ ማሽኖችና የእንጀራ መጋገሪያ የኤሌክትሪክ  ምጣዶች ከበቂ የሰው ኃይል ጋር በማዘጋጀት በቀን 20ሺ እንጀራ እና 45ሺ ዳቦ በማምረት በራሳቸዉ ትራንስፖርት  በየት/ቤቶች እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት  ኃላፊ በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የመጋቢ እናቶችን ድካም መቀነስ ሲሆን ሌላው ዘይትና ስኳር እንደዚሁ ከአንድ ማእከል እዲያገኙ ከሸማች ህብረት ስራ ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸዉን መግለጻቸዉን ከክፍለ ከተማዉ ት/ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።