በትምህርት ቤቶች ለኮቪድ 19 በሽታ መከላከል የሚውል የ1.5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ፡፡
ኮርዲያድ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ደርጅት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውል አንድ መቶ ሰማንያ ሺ ለህጻናት እና 39 ሺ ለአዋቂ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ፣ ዘጠና ስምንት የሙቀት መለኪያ ማሽን እና ስድስት ሺ ሳኒታይዘር ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልፅዋል፡፡ የቢሮው ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በቁሳቁስ ርክክቡ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው እንደገለፁት የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የብዙ አካላት ተሳትፎን በማካተት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው በዛሬው እለት ገብሬኤልዋ የህፃናትና ሴቶች በጎ አድራጎት ደርጅት አማካኝነት ኮርዲያድ በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለተደረገው ድጋፍ በትምህርት ቢሮ እና በተማሪዎች ስም አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
የገብሬኤልዋ የህፃናትና ሴቶች በጎ አድራጎት ደርጅት ሀላፊ ቤዛ ሃይለማሪያም በበኩላቸው እንደገለፁት ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ ለብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋትና ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለ ወረርሽኝ ነው ብለዋል፡፡ ህይወትን ከማጥፋት በሻገር የትምህርት ሂደትን በማስተጓጎል በርካታ ተማሪዎች እቤት እንዲቀመጡ በማድረጉና አሁን የተጀመረውን የመማር ማስተማር ስራ ለማገዝ በአንድ ነጥብ አምስት ሚለዮን ብር ወጪ የሚገመት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣የሙቀት መለኪያ ማሽን እና ሳኒታይዘር ድጋፍ መደረጉን በመግለጽ በድርጅታቸዉ ጥያቄ መሰረት ኮርዲያድ ግብረ ሰናይ ደርጅት ድጋፉን በመስጠቱ ድርጅቱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል ፡፡ አክለውም ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ የመስራትና ለተማሪዎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!