ቀን 19 / 09 / 2012 ዓ/ም

  1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ስአት 1፡30 እንዲሆን የተቀመጠ ሲሆን መዉጫ ስአቱም 9፡30 እንዲሆን ተደርጎ ተሸጋሽጓል፡፡ ይህም የትራንስፖርት መጨናነቅን ለመቀነስ ነው፡፡
  2. ከቤት ዉጭ በማንኛዉም ቦታ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግን ግዴታ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
  3. አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች መደበኛ የወንበር አቅማቸዉ ከ45(አርባ አምስት) ሰዉ በላይ የሆነ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ከመደበኛ ዋጋዉ 75% እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን መደበኛ የወንበር ቁጥራቸዉ እስከ (45) አርባ አምስት ሰዉ የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ደግሞ 100% መሆኑ ተወሰኗል፡፡
  4. በኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረዉ ክልከላ ተነሰቶ አጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያስችል አማራጭ ክልከላ እንዲተገበር የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወስኗል፡፡

ሙሉ ዝርዝሩን ቀጥሎ ይመልከቱ ፡፡

ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በወቅታዊው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ የተሰጠ የፕሬስ መግለጫ

በአገራችን የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት እለት ጀምሮ በመንግስትና በባለድርሻ አካላት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን ትዕዛዞች፣ ክልከላዎችና መልዕክቶች እየተላለፉ ነዉ፡፡ እነዚህን መልእክቶችና ትእዛዞች ሰምቶ ለራስ በመፈጸምና ሌሎችን እንዲፈፅሙት በማድረግ በኩል በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሻሉ ሁኔታዎች ቢኖሩም ነገር ግን በርካታ በሚባለዉ ህብረተሰቡ ዘንድ የመዘናጋት፣ የቸልተኝነትና በሽታዉን አስመልክቶ የሚሰጡ ትእዛዛቶች ወደ ጎን በመተዉ የሚሰጡ መግለጫዎችን የመላመድና ትኩረት ያለመስጠት ሁኔታዎች እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

በቅርቡ በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶችና በግል ተቋማት ወሰጥ ያደረግነዉ ምልከታ ከቅደመ ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ የመዘናጋት፣ ትኩረት ያለመሰጠት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ማህበረሰባችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተለይም በግብዒት ቦታዎችና በትራንስፖርት አገልግሎት መሰጫ አካባቢ እያሳየ ያለዉ መዘናጋትና ህጎቹን ያለማክበር ጉዳይ አሳሳቢ ነዉ፡፡

ይህ የኮሮና ቫይረስ በአገራችን በተገኘበት እና የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ሰሞን የነበሩ ጥንቃቄዎች ጋር ሰነጻጸር እየቀነሰ መዘናጋት እየጨመረ ሲሆን በተቃራኒዉ አሁንም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ እጅጉን አሳሳቢና ዋጋ የሚያስከፍል ጉዳይ እየሆነ ይገኛል፡፡

መንግስት በሽታዉን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዉጆ ደንብና መመሪያዎችን በማዉጣት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ከዚህ ቀደም የወጡ መመሪያ ቁጥር 1/2012 እና መመሪያ ቁጥር 2/2012 ማሻሻያዎችን የያዘ መመሪያ ቁጥር 4/2012ን አፅድቆ ስራ ላይ እንዲዉል አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረትም በመመሪያ ቁጥር 4 በኮድ 2 የቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ የነበረዉ ከፊል የእንቅስቃሴ ክልከላ፣ የማሰክ አጠቃቀም፣ በአገር አቋራጭ የህዝብ ተሸከርካሪዎች ላይ እንዲሆም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች መግቢያና መዉጫ ስአት ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

የኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ላይ መጣል ሚገባው የትራንስፖርት ሚኒስቴር በኩል የተደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ በከፊል በመገደብ ግለሰቦች ቤታቸዉ እንዲዉሉ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ ተድርጎ በሙሉና በጎዶሎ መለያ ቁጥር ከፊል እገዳ ተጥሎ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ሆኖም የኮድ 2 ተሸከርካሪ ባለቤቶች በታሰበዉ መልኩ ቤታቸዉ ከመዋል ይልቅ የህዝብ ትራንስፖርት በመጠቀም እና ታርጋዎችን እየቀያየሩ የመጠቀም ሁኔታ መታየቱ እንዲሁም ተራቸዉ ባልሆነ ቀን ቤታቸዉ ከመዋል ይልቅ በሰፊዉ የመንቀሳቀስ ሁኔታ የተስተዋለ በመሆኑ ክልከላዉን መልክ መቀየር አስፈላጊ ሆኗል፡፡

በመሆኑም በአጠቃላይ በኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረዉ ክልከላ ተነሰቶ አጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያስችል አማራጭ ክልከላ እንዲተገበር የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወስኗል፡፡

ከእንቅስቃሴ መቀነሻ አሰራሮች አንዱ የሆነዉ በሀገር አቋራጭ ተሸከሪካሪዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ነው፡፡

የዋጋ ጭማሪ ማድረግም ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ለመገደብ አሰተዋጽኦ እንደሚያደርግ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የተደረገው ጥናት ያመላክታል፡፡

በዚሁ መሰረት አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች መደበኛ የወንበር አቅማቸዉ ከ45(አርባ አምስት) ሰዉ በላይ የሆነ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ከመደበኛ ዋጋዉ 75% እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን መደበኛ የወንበር ቁጥራቸዉ እስከ (45) አርባ አምስት ሰዉ የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ደግሞ 100% መሆኑ ተወሰኗል፡፡

በተያያዘ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት የማስክ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከቤት ዉጭ በማንኛዉም ቦታ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግን ግዴታ እንዲሆን ወስኗል፡፡ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ ማሰክ በፋብሪካዎች የተሰራ ወይም ባህላዊ ጨርቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ግዴታ በማሰፈጸም ረገድ የጸጥታ መዋቅሩ ኃላፊነት እንዳለበት ተወሰኗል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ስአት 1፡30 እንዲሆን የተቀመጠ ሲሆን መዉጫ ስአቱም 9፡30 እንዲሆን ተደርጎ ተሸጋሽጓል፡፡ ይህም የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመቀነስ ነው፡፡

በአጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት በመሆኑ የሚታዩ መዘናጋቶችን እና ችላ ባይነትን በመቅረፍ ሁላችንም ህግና ሥርዓቱን ማክበር ግዴታ እንደሆነ በመገንዘብ መላዉ የሀገራችን ህዝብ እራሱ፣ቤተሰቡንና ሀገሩን የኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትለው ጉዳት ለአፍታም ሳይዘናጋ ለመጠበቅ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

ቀን 18 / 09 / 2012 ዓ/ም

የኮረና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ መንግስት ያስቀመጠውን የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ አራት ትምህርት ቤቶች ለአንድ አመት የእውቅና ፍቃዳቸው መታገዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ አለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነው የኮረና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ትምህርት ሚኒስተር ከመጋቢት 7/2012 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በወሰነው መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ  የግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት አገልግሎታቸውን በተለያዩ መንገዶች እንዲሰጡና የሚያስከፍሉት የአገልግሎት ክፍያም ከ50 እስከ 75 ፐርሰንት እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

ወይዘሮ ሸዊት አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መመሪያው ተግባራዊ መሆኑን በትምህርት ቤቶቹ ክትትል ማድረጉንና አብዛኞቹ በወረደው መመሪያ መሰረት ተገቢውን ክፍያ በማስከፈል ላይ መሆናቸውን በመግለጽ 21 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከመመሪያው ውጪ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ በመጠየቃቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ማስተካከያ እንዲያደርጉ በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት 17 የሚሆኑት ማስተካከላቸውን ጠቁመው ቀሪዎቹ 4 ትምህርት ቤቶች ግን የክፍያ መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ ስላልሆኑ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አገልግሎት እንዳይሰጡ ለአንድ አመት እውቅና ፍቃዳቸው መታገዱን አስታውቀዋል፡፡

ፍቃዳቸው የታገደባቸው ትምህርት ቤቶች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙት ለምለም እና ሮማን ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ስሪ ኤም አካዳሚ ና አራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ገነት መሰረተ ክርስቶስ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን በመግለጫው ጠቅሰዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

ቀን 17 / 09 / 2012 ዓ/ም

Excerpt from the speech by Haile Selassie I, Emperor of Ethiopia, May 1963

“We stand today on the stage of world affairs, before the audience of world opinion. We have come together to assert our role in the direction of world affairs and to discharge our duty to the great continent ..

… Africa is today at mid-course, in transition from the Africa of yesterday to the Africa of Tomorrow. Even as we stand here, we move from the past into the future. The task on which we have embarked, the making of Africa, will not wait. We must act, to shape and mold the future and leave our imprint on events as they slip past into history…..

…. Those men who refused to accept the judgment passed upon them by the colonizers, who held unswervingly through the darkest hours to a vision of an Africa emancipated from political, economic and spiritual domination, will be remembered and revered wherever Africans meet. ….

……If we permit ourselves to be tempted by narrow self –interest and vain ambition, if we barter our beliefs for short-term advantage, who will listen when we claim to speak for conscience, and who will contend that our words deserve to be heeded? We must speak out on major world issues, courageously, openly and honestly, and in blunt terms of right and wrong. If we yield to blandishments or threats, if we compromise when no honorable compromise is possible, our influence is weakened.

Read the full speech made in 1963 https://au.int/en/overview

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

ቀን 17 / 09 / 2012 ዓ/ም

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2844 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባ ሶስት (73) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት (655) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባት (7) ሰዎች (4 ሰዎች ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል እና 1 ሰው ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ (159) ነው።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=CZYnhP3JRe8

ቀን 16 / 09 / 2012 ዓ/ም

በ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር በአጭር የፅሁፍ መልእክት ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሙሉ ዝግጅቱን ሊንኩን በመጫን ይከታተሉ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

ቀን 15 / 09 / 2012 ዓ/ም

እናመሰግናለን ! አብዝቶ ይስጥልን !

 ት/ቤቶች ማህበራዊ  ኃላፊነታቸዉን ከመወጣት አንፃር አርአያነት ያለው ተግባር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፈለ ከተማ  አባይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሚገኙ  መምህራንና የአስተዳደር  ሰራተኞች ለ 65 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የተማሪ ወላጆች በጥሬ ገንዘብ ፣ የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ  ድጋፍ አድርገዋል።

በድጋፉ ወቅት የተገኙት የክፍለ ከተማችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ካሳሁን የትምህርት ተቋማትና ሰራተኞች  እያደረጉት ያለው መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። አቶ ፍቃዱ አክለውም የመጣብንን የተፈጥሮ አደጋ ለመከላከል ሁሉም በያለበት ሊረባረብ ይገባል ። ይህ ክፉ ቀን ያልፋል ሁላችንም ካለን እናካፍል መምህራን የሁላችንም አርያ ናችሁ በርቱ እንበረታለን ሲሉ በአስተዳደሩ ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ።

በዚሁ ከፍለ ከተማ  በወረዳ 05 እና 02 አስተዳደር ስር የሚገኙት  ዴስትኒ አካዳሚ እና የኔታ አካዳሚ ገቢያቸው አነስተኛ ተብለው ለተለዩ 180  አባወራዎችና እማወራዎች ከ 180 ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና የተለያዪ ምግቦችን የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

ቀን 15 / 09 / 2012 ዓ/ም

 ኢድ ሙባረክ !

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1441 አመት ሂጅራ የኢድ አልፍጥር በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ይህን በአል ስናከብር በአለማችን ፣ በሀጉራችን እንዲሁም በሃገራችን  የተከሰተዉን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተጋፈጥንበት ወቅት ስለሆነ አስፈላጊዉን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ ፣ በመረዳዳትና ወረርሽኙን እንዳስወግድልን አላህን በመለመን ሊሆን ይገባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

ቀን 14 / 09 / 2012 ዓ/ም

በ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቭዥን ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በየእለቱ የሚቀርቡ ትምህርቶችን የ you tube  አድራሻችን https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ ሳብስክራይብ በማድረግ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

 Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

በ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር በአጭር የፅሁፍ መልእክት ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ፣ በኤፍ ኤም 94.7 ሬዲዮና በሌሎች የኢንተርኔት አማራጮች ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እየተሰጠ ባለው ትምህርት በተለይም ድግሞ በትምህርት በቤቴ መርሃ ግብር ላይ የተማሪዎችን ተሳትፎ ለማጠናከርና በትምህርታቸው እውቀት መገብየታቸውን ለመለካት ሲካሄድ በነበረዉ የ8455 የሽልማት መወዳደሪያ መልዕክት መላኪያ ላይ የአሸናፊ ተማሪዎች ሽልማት መርሃ ግብር ዛሬ ግንቦት 13/2012 ዓ/ም ተካሄደ፡፡ 

በተካሄደው መርሃ ግብር ከ7ኛ –12ኛ ክፍል ላሉ 30 አሸናፊ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር እና ለ11 ልጆቻቸዉን ለዚህ ላበቁ ቤተሰቦች የ43 ኢንች ቴሌቪዥን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

በሽልማት መርሃ ግብሩ ተገኝተው ሽልማቱን ያስጀመሩትና መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ (ኢ/ር) ታከለ ኡማ እንደገለፁት አዲስ አበባን ከሚመጥን ተግባር  መካከል  ትውልድን በትምህርት መገንባትና ተገቢውን ተግባር በመፈፀም በትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ልዩነት በማስተካከል  በመንግስት ትምህርት ቤት መማር ኩራት መሆኑን በስራ ማሳየት ነው ብለዋል፡፡  አክለውም ለዚህ ደግሞ በተማሪዎችና በመምህራን ላይ ኢንቨስትመንት በመጨመር በተማሪዎች አልባሳት( ዩኒፎርም ) ፣ በምገባ መርሃ ግብር ፣ በትምህርት መማሪያ ግብአቶች እና መስል የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በአዲስ መልክና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡ በተያዘው አመት ለ300ሺህ ተማሪዎች እየተደረገ ያለው “የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር” በቀጣዩ አመት 600 ሺህ ተማሪዎች የሚካተቱበት ይሆናል ሲሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ ጨምረዉ ተናግረዋል።

የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም  ሙላቱ የትምህርት መርሃ ግብሩ እንዲሳካ ከፍተኛ  አስተዋጽኦ ላደረጉ የከተማው  አስተዳደር ፣ በየደረጃው ላሉ የትምህርት ቢሮ አመራሮችና የትምህርት ባለሙያዎች፣ ለአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሌሎች በትምህርት ቢሮ ስም አመሰግናለሁ  ብለዋል፡፡

ቀን 12/ 09 / 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ8ኛ ክፍል ፊዚክስ ሞዴል ፈተና የቀረበ በመሆኑ ተማሪዎች ተገቢዉን ዝግጅት በማድረግ እንድትጠብቁ እየጠየቅን ለፈተናዉም 2 ሰሃት የተሰጣችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ Biiroo Barnoota magaalaa finfinneetti Qormaanni Fiizksii kutaa 8ffaa waan gadhiifameef akka qoramtan beeksisaa Qormaataaf sa’aatti 2:00 isinnif kennameera . መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ እና የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! You Tube: https://www.youtube.com/channel/UCMoKzm9xgyid8CYTbh4-Ckw/ Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡

888