የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን የኢ ስኩል (e-school ) ሲስተም ሶፍትዌርን ከሚያለማው ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናው የኢ ስኩል (e-school)ሲስተም ሶፍትዌር በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ከሚደረግባቸው የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን ሱፐርቫይዘሮችና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የትምህርት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም ትሪያ ሶሊሽን/TRIA SOLUTION/ በተሰኘውና ሶፈትዌሩን በማልማት ላይ ከሚገኘው ካምፓኒይ በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ነው የተሰጠው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው የኢ -ስኩል ሲስተሙ ሶፍትዌሩን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት አገልግሎቱን ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን በማሰብ መዘጋጀቱን ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊዎችም ሶፍትዌሩን ከሚያለማው ድርጅት በመጡ ባለሙያዎች ከሶፍትዌሩ አተገባበር ጋር በተገናኘ የሚሰጠውን ገለጻ መሰረት በማድረግ በየትምህርትቤቶቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ በበኩላቸው ስልጠናው በዋናነት ሶፍትዌሩ በሙከራ ደረጃ ትግባራዊ ከሚደረግባቸው 20 የሚሆ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን ሱፐርቫይዘሮችና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የትምህርት ባለሙያዎች መዘጋጀቱን ጠቁመው ስልጠናውም ከሶፍትዌሩ አተገባበርና አጠቃቀም ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የትምህርት ስርአቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግን ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡
የኢ-ስኩል ሲስተሙ በስሩ የተለያዩ ንዑሳን ሲስተሞች እንዳሉትና ሲስተሙም በዋናነት የወረቀት ስራን በመቀነስ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪው አቶ ደረጀ ዳኜ ገልጸው በቀጣይ ሶፍትዌሩን ከሚያለማው ካምፓኒ ጋር በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ሂደቱንም ሆነ የትምህርት መረጃ አያያዝ ስርአቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/