ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ አፈጻጸም በትምህርት መሻሻል መርሃግብርና በተማሪዎች ፈተና

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተማችን ባለፉት 5 አመታት የተለያዩ ተግባራት ስታከናውን ቆይታለች፡፡ የትምህርት ጥራት ፓኬጅ ስድስት ፕሮግራሞች ሰተገብር የቆየ ሲሆን በትምህርት መሻሻል በርሃግብርና በተማሪዎች ፈተና ዙሪያ  አፈጻጸሙ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የትምህርት ቤት መሻሻል በርሀ ግብር

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው ጥራት ያለው ትምህርት የማዳረስ ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የትምህርት መዋቅሩ አስተማማኝ መልካም አጋጣሚ እንዳሉት ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ባሁኑ ግዜ በተጠናከረ ሁኔታ ተደራጅቶ የገባው የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት (ወተመህ) መውሰድ ይቻላል፡፡ ትምህርት ቤቶች በስታንዳርዱ መሰረት በማደራጀት ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ያሉበት ደረጃ በግምገማ ተለይቶ ደረጃ እየተሰጣቸው የማስኬድ አግባብ ላይ ተደርሷል፡፡

ይሁን እንጂ ባሁኑ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ የሚያሳዩትን ፍላጎት አውን ለማድረግ በትምህርት ስራው ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ የተለያዩ የንቅናቄ መድረኮችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡በመሆኑም የኀብረተሰቡ ተሳትፎና አጋርነት ታክሎበት ህዝቡ ለትምህርት ስራ ያለውን ባለቤትነት የበለጠ በማጠናከር የፋይናንስና የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ፣ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት፣ነባሮቹንም በማደስ፣ የትምህርት ግብአቶችን በሟሟላት ረገድ ተገቢውን ተሳትፎ በማድረግ አጋርነቱንና ባለቤትነቱን አንዲያረጋግጥ ማስቻል ተገቢ ነው፡፡

ት/ቤቶች ተፈላጊውን የብቃት ደረጃ ማሟላታቸውን በመገምገም ብቃታቸው የተረጋገጠላቸው ብቻ ዕውቅናና ዕድሳት እያገኙ የሚሰሩበት ህጋዊነት ያለው ሥርአት በመዘርጋት በተቋማት መካከል መልካም የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር ከማድረግ አንፃር በከተማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ደረጃ ምደባና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን በጥራት የመምረጥና ዕውቅና የመስጠት፣ከተፈላጊው ደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ክፍተታቸውን በማሳየት በቀጣይ ወደ ተሻለ ደረጃ መድረስ እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተፈላጊ ግብ የሆነውን የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር እንዲያሻሽሉ የማድረግ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል::

በ2006 ዓ.ም በተደረገው የ20% የውጭ ኢንስፔክሽን ትግበራ በተደረገው መሠረት በከተማችን የሚገኙ 243 የመንግስትና የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ 39 (21%) የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች እና 13(23%) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ ሶስት ወይንም ደረጃውን ያሟሉ ሲሆኑ፣127(68%) የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች እና 37 (66%) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በደረጃ ሁለት ላይ በመሆናቸው በመሻሻል ላይ የሚገኙ እንዲሁም 21(11%) የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች እና 6(11%) የሁለተጃ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ አንድ ማለትም ደረጃውን ያሟሉ ናቸው፡፡በሁለቱም የትምህርት ደረጃ እርከን ላይ ደረጃ 4 ሆኖ ደረጃውን በከፍተኛ ደረጃ ያሟላ ተቋም የሌለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ከዚህ አንፃር በደረጃ አንድና ሁለት የሚገኙ የትምህርት ቤቶቻችን መብዛትና በደረጃ 4 ላይ የተፈረጀ ትምህርት ቤት አለመኖር ትምህርት ቤቶቻችን ስታንዳርዱ ጠብቀው እንዲደራጁ ማድረግ ላይ ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ያሳያል፡፡

የተማሪዎች ውጤት

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ ግብር ተቀይሶ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ፡፡ የመርሃ ግብሩ ዋና አላማ የተማሪዎችን ውጤትና አስተሳሰብ ማሻሻል ነው፡፡መርሃ ግብሩን ተግባራዊ በማድረግ በመጀመርያ ደረጃ የክህሎት መሻሻል ማሳየት ጀምሯል፡፡

በ10 ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት የአዲስ አበባ 2.00 ነጥብና በላይ በመቶኛ

4

 

ከመረጃው መረዳት እንደሚቻለው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና(10ኛ ክፍል) ውጤት ወጣ ገባነት ያለው ነው፡፡ ውጤቱም በተከታታይ አመታት ሴቶች ከወንዶች ብልጫ ያላቸው ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከሃገር አቀፍ ጋር ሲነጻጸር አበረታች ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ከ10ኛ ክፍል ወደ መሰናዶ ያለፉ (ከ 2003-2006 ዓ.ም)

5

የ2ኛ ደረጃ የመጀመርያው ሳይክል ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ካለፉ የወደፊት ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው የሚያመቻቹበት እና መሰረት የሚጥሉበት በመሆኑ ከ2003 ዓ.ም ከነበረው 58.9% በ 2006 ዓ.ም ወደ 66.84% በ 7.7% የጨመረ መሆኑን ያሳያል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተና 50% (350 እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ከ2003-2006 ዓ.ም)

6

የ2ኛ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን የሚገቡበት እንደመሆኑ መጠን ከ2003 ዓ.ም ከነበረበት 40.2% በ 2006 ዓ.ም ወደ 40.16% በ 0.04 የቀነሰ መሆኑን ያሳያል፡፡ በጾታ ደረጃ ስናየው ላለፉት 4 ተከታታይ የትምህርት አመታት ወንዶች ከሴቶች የበለጡ እንደሆኑ ነው፡፡

የክልላዊ ፈተናን በተመለከተ

ከ8ኛ ክፍለ ወደ 9ኛ ክፍ የተዛወሩ ተማሪዎች ብዛት (ከ 2003-2006 ዓ.ም)

7

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ 2003 ዓ.ም ከነበረበት 72.0% በ2006 ዓ.ም ወደ 67.6% በ 4.4% ዝቅ ብሏል፡፡ በሴት እና በወንድ ተማሪዎች መካከል ስንመለከት ሴቶች ከወንዶች በተሸለ ደረጃ ወደ 9ኛ ክፍል የተሸጋገሩ ሲሆን በ 2003 ዓ.ም ከነበረው 4.4% የሴቶች ብልጫ በ 2006 ዓ.ም ወደ 6% ከፍ ብሏል፡፡

የትምህርት ሽፋን፡ ተደራሽነት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነትን በቅድመ መደበኛ ትምህርት

ለማድረስ በርካታ ሥራዎች ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዙሪያ በቅድመ መደበኛ ትምህርት የግል ባለሃብቶች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከአጠቃላይ የዘርፉ እንቅስቃሴ ሲታዩ ድርሻው የላቀ መሆኑ ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል በከተማው በሚገኙ የግል ተቋማት ከፍለው መማር የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በቅድመ መደበኛ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመንግስት የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች ይህን ፕሮግራም ተግባራዊ ተደርጓል ፡፡ ባለፉት ዓመታት ከፍለው ማስተማር ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በመንግስት ት/ቤቶች በተዘረጋው የቅድመ መደበኛ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም ከአጠቃላይ ተጠቃሚዎች ብዛት አንጻር ሲታይ ግን በቀጣይ ብዙ ሥራ መሥራት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

1

በ 2003 ዓ.ም የእቅድ መደበኛ ተቋማት ብዛት 998 የነበረ ሲሆን በ 2007 ዓ.ም 1092 ለማድረስ ተችሏል፡፡ ይኸውም የ8.6% ዕድገት አሳይቷል ፡፡ ይሁን እንጂ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን የማጠቃለያ አመት 1200 ተቋማት ይከፈታሉ ተብሎ የታቀደ ቢሆንም የተከፈተው 1092 በመሆኑ አፈፃፀሙ 91% ደርሷል፡፡ በ 2003 ዓ.ም የመንግስት ቅድመ መደበኛ ተቋማት ብዛት 51 ሲሆን በ 2007 ዓ.ም 202 ለማሣደግ ተችሏል፡፡በተጨማሪም ቅድመ መደበኛ መክፈት ባልተቻለባቸው የመንግስት ት/ቤቶች የ “ኦ” ክፍል በመክፈት 6 አመት የሞላቸው ህጻናት አንድ ዓመት ዝግጅት በማድረግ አንደኛ ክፍል እንዲገቡ ለማድረግ የተቻለ ሲሆን የ ኦ ክፍል ተቋማት 66 ሲሆን አጠቃላይ ባለፉት አመታት መንግስት የቅድመ መደበኛ የትምህርት ተደራሽነት ለማሳደግ በሚያስችል መንገድ ለመፈፀም አቅዶ እየሰራ በመሆኑና በተጨማሪም የግል ባለሀብቶች በየዘርፉ ባደረጉት ከፍተኛ ለውጥ ተመዝግቧል፡፡

2

በ 2003 ዓ.ም የቅድመ መደበኛ አጠቃላይ የተማሪዎች ቁጥር 118840 የነበረ ሲሆን በ 2007 ዓ.ም ወደ 157475 አድጓል ይህም ባለፉት 5 አመታት 24.5 % ዕድገት አሳይቷል ፡፡በሌላ በኩል ከላይ ከቀረበው አጠቃላይ የተማሪዎች ብዛት አኳያ በ 2007 ዓ.ም በመንግስት ቅድመ መደበኛ ተማሪ 35531 (22.55%) ሕጻናት እየተማሩ ይገኛል፡፡

የቅድመ መደበኛ ጥቅልና ንጥር ተሳትፎ

3

የቅድመ መደበኛ ጥቅል ተሣትፎ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን አመን ዕቅድ 100% ለማድረስ ቢሆንም ማከናወን የተቻለው ግን 92.8% ነው፡፡ የታቀደውን ያህል ማከናወን ያልተቻለበት ምክንያት፣ የአፀደ ሕፃናት መማርያ እድሜ ከ 4-6 ዓመት መሆኑ ቢታወቅም በተግባር ግን ዕድሜያቸው 6 አመት የሆኑ ሕፃናት 1ኛ ክፍል በመግባታቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ንጥር ቅበላ በተመለከተ በ 2003 ዓ.ም 68% የነበረ ሲሆን በ 2007 ዓ.ም 79.64% ማድረስ ተችሏል ፡፡ ይኸውም በ 2007 ዓ.ም በቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በመማሪያ ዕድሜያቸው (ከ4-6 ዓመት) ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ በመማር ላይ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ነገር ግን ንጥር ተሳትፎ 100% ማድረስ ያልተቻለው ሕፃናት ከ3 ዓመት ጀምሮ ት/ቤት እየገቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

መግቢያ

አገራችን በነደፈችው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ህዝባችንን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለማላቀቅ በትምህርትና ስልጠና ለመለወጥ ሁሉም ዜጎች የትምህርት እድል ተጠቃሚ መሆን አለባቸው መንግስትም የዜጎችን አቅም በትምህርት ስልጠና የማጎልበትን አስፈላጊነት በጽኑ አምኖ በወሰዳቸው እርምጃዎች በጥቂቱ ዐመታት ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ የትምህርት አቅርቦትን በማስፋፋት ብዙ የተጓዝን ቢሆንም አሁንም የትምህርት ዕድል ያላገኙ ዜጎች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ከቦታ ቦታ ያለውን ያለመመጣጠን በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የተሳትፎ ልዩነት ለማጠበብ ቀላል የማይባሉ ተግባሮች ተከናውነዋል፡፡

ራዕይ

በአዲስ አበባ ከተማ ውጤታማ የትምርት ሥርአት መማስፈን በ 2012 እ.ኤ.አ ዓለም ዓቀፋው ተወዳዳር የሆኑ የትምህርት ተቋማት በልማት በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ስብዕና ያላቸው ዜጎች ማፍራት፡፡

ተልዕኮ

የአዲስ አበባ ከተማን ነዋሪ በትምህርት ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ ለትምህርት መዋቅሩ አካላትላ በትምህርት መስክ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት፡አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር የትምህርት ተቋማትን በፍትሐዊነት በማስፋፋት የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ አለምአቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት በተስማሚ ፕሮግራሞች ለህብረተሰቡ ማድረስ፡፡

እሴቶች

  • ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን
  • በመልካም ሥነምግባር የታነጹ ዜጎችን እንፈጥራለን
  • ፈጠራና ችግር ፈቺነት አናበረታታለን
  • በጥናትና ምርምር የትምህርት ችግሮቻችን እንፈታለን
  • በእውቀትና በ እምነት እንሰራለን
  • ግልጽነት
  • ተጠያቂነት
  • ለለውጥ ዝግጁ ነን
  • የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን
  • በጋራ መስራት