የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የግብዓት ድጋፍ ለመርሳ 2ኛ ደ/ት/ቤት አደረገ::
የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት በሰሜን ወሎ ዞን ለሚገኘዉ እና በጦርነቱ ምክንያት የወደመዉን መርሳ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለማቋቋም እንዲቻል ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የግብዓት ድጋፍ አድርጋል፡፡
ጽፈት ቤቱ በስሩ ከሚገኙ ከ7ቱ 2ኛ ደ/ት/ቤቶች ያሰባሰበዉን ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ግብአት ድጋፍ ማድረጉን አሳውቃል::
ድጋፋን የሀብሩ ወረዳ ት/ፅ/ቤት ሀላፊ፣ የመርሳ 2ኛ ደ/ት/ቤት ር/መምህራን፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት ከየካ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ተረክበዋል::
የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዉ ት/ቤቱ ሙሉ በሙሉ የወደመ መሆኑን ፣ የላብራቶሪ ፣ አይሲቲ ፣ የቤተ መፅሀፍት፣ የፕላዝማ እና ሌሎችም ግብዓቶች ሙሉ ለሙሉ መዘረፉቸዉን እና መውደማቸዉን መመልከቱን ገልጻል::
የሀብሩ ወረዳ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊ እና ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ምንም አይነት ድጋፍ እንዳልተደረገ በመግለጽ ለችግራችን ቀድሞ ለደረሰዉ ለየካ ክ/ከተማ አስተደዳር ት/ፅ/ቤት እና ለ2ኛ ደ/ት/ቤቶች ምስጋና ካቀረቡ በሀላ አሁን በተደረገላቸዉ ድጋፍ ትምህርት ቤቱን ትምህርት ለማስጀመር እንደሚችሉ ማሳወቃቸዉን ከየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
















