ቀን 20/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም የ6 ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ፡፡

ምዘናው እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነነት ሲካሄድ ቆይቶ ዘንድሮ በእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እንዲመራ በተወሰነው መሰረት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ትምህርት ቢሮ ድረስ አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ የሚካሄድ ሲሆን  ቀደም ሲል ከ400 በላይ ለሚሆኑ መዛኞችና አስተባባሪዎች በምዘናው ሂደትና ለመመዘኛነት በተዘጋጁ መስፈርቶች ዙሪያ ኦረንቴስን መሰጠቱ  ይታወቃል፡፡ 

ምዘናው በዛሬው እለት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረ መሆኑን እና ከነገ ጀምሮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንደሚመዘኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸው በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ከማስቻሉ ባሻገር በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት  እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 Blog: – https://aacaebc.blogspot.com

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 16/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል ሴክተሩን በአመራርነት አገልግለው ወደ ሌላ ዘርፍ ለሄዱ አመራሮች የሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

ሽኝቱ የተደረገላቸው ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ለአቶ ሳመሶን መለሰ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ ለቆዩት አቶ አለልኝ ወልዴ ሲሆን በሽኝት መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት እና የፕሮሰስ ካውንስል አባላትን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በሽኝት ፕሮግራሙ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው እለት የሚሸኙት አመራሮች በትምህርት ሴክተሩ በነበራቸው ቆይታ በሴክተሩ ለተመዘገበው ውጤት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው አሁን በተመደቡበት ዘርፍም ለትምህርት ሴከክተሩ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን በመግለጽ በተመደቡበት ሴክተር መልካም እድል እንዲገጥማቸውና በስራቸውም ውጤታማ እንዲሆኑ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሽኝቱ የተደረገላቸው አቶ ሳምሶን መለሰ እና አቶ አለልኝ ወልዴ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ለተደረገላቸው የክብር ሽኝት ላቅ ያለ ምስጋና  በማቅረብ በትምህርት ሴክተሩ በነበራቸው ቆይታ ያካበቱት የስራ ልምድም ሆነ በጋራ የመስራት ባህል አሁን በተመደቡበት ሴክተር ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዛቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 15/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም የ6ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ለሚያካሂዱ መዛኞች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡

ምዘናው እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነነት ሲካሄድ ቆይቶ ዘንድሮ የምዘና ስርዓቱ በእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እንዲመራ በተወሰነው መሰረት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ትምህርት ቢሮ ድረስ አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን  በኦረንቴሽኑ ከ400 በላይ መዛኞችና አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ 

በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ከማስቻሉ ባሻገር የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸው በምዘና ሂደቱ በመዛኝነት የሚሳተፉ የትምህርት ባለሙያዎችም ሆኑ አመራሮች ለምዘናው የተዘጋጁ የመመዘኛ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ምዘናውን ማካሄድ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ምዘናው ከነገጀምሮ በሁሉም የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የወረዳና ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ጨምሮ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሚገኙ የስራ ክፍሎች የሚካሄድ ሲሆን ተመዛኝ ተቋማትም መዛኞች ለምዘና በሚሄዱበት ወቅት ተገቢውን መረጃ በማቅረብ ለምዘና ስርአቱ ውጤታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 14/6/2015 ዓ.ም

የዝውውር ማስታወቂያ!

በአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ (የሀገር በቀል 2ኛ ቋንቋ) የብዙሃ ቋንቋ በከተማዋ ባሉ ትምህርት ቤቶች ለመተግበር በተቀመጠው ውሳኔ መሰረት የዝውውር ማስታወቂያ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ የትምህርት አይነቶች በዲግሪና በዲፕሎማ የተመረቁ ብቻ በኦን ላይን /ONLINE/ በተገኘው መረጃ መስፈርቱን አሟልታችሁ ስም ዝርዝራችሁ በትምህርት ቢሮው ድግረ ገፅ በቴሌግራም የተለቀቀላችሁ ብቻ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መምህራን ትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 408 የትምህርት ማስረጃችሁንና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ  ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ብቻ በአካል በመቅረብ የዝውውር ደብዳቤ እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ከላይ ከተጠቀሱት የትምህርት አይነቶች ማለትም አማርኛና አፋን ኦሮሞ ዲግሪና ዲፕሎማ ብቻ ከነዚህ ትምህርት ዓይነቶችና ትምህርት ዝግጅት ውጪ ተቀባይነት የለውም፡፡
  • ዝውውሩ የሚመለከታቸው በክልሎች በመንግስት ትምህርት ቤቶች በስራ ላይ ያሉ መምህራንን ብቻ ነው፡፡
  • ደብዳቤ ለመውሰድ ወደ ት/ቢሮ ስትመጡ ደብዳቤ የሚፃፍላችሁ ለክልል ወይም ለዞን ወይም ለወረዳ ት/ጽ/ቤት እንደሆነ ወስናችሁ  እንድትመጡ፡፡
  • ስማችሁ ከላይ  የተለቀቀላችሁ ከአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ የትምህርት ዓይነቶችና ከዲፕሎማና ዲግሪ ምሩቃን ውጪ የሆናችሁ መምህራን ዝውውሩ የማይመለከታችሁ በመሆኑ ትምህርት ቢሮ መምጣትና ደብዳቤ መውሰድም አይጠበቅባችሁም፡፡ ከዚህ ውጪ በሆኑ ትምህርት ዓይነትና ዝግጅት ያላችሁ መምህራን ለሚፈጠርባችሁ እንግልት ት/ቢሮው ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Beeksisa jijjirraa!

Biiroon Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee Manneen Baruumsaa Magaalaa Finfinnee keessatti argaman hunda keessatti Afaan dhalootaa irratti dabalataan Afaan biyya keessaa tokko akka baratamu murtaa’un isaa ni beekkama.

Haaluma kanaan beeksiisa jijjirraa barsiisotaa  Gosa barnotaa Afaan Oromoofi Afaan Amaariffaan Sadarkaa barnootaa Dippiloomaafi Digiirii  qofaan Online irratti akka galmooftan gadi dhiifamuun isaa ni yaadatama. Akkaatuma kanaan barsistootni galmooftanii callallii dabartanii maqaan keessan liinkii armaan gadii irratti caqafame Guyyaa beeksifni kun bahe irraa eegalee guyyaa hojii 10(kudhan) Keessatti qofa Waraqaa Eenyummaa keessan ibsuufi ragaa baruumsaa keessan qabachuun Biiroo barnoota bulchiinsa magaaalaa Finfinneetti darektoreetii misooma barsiisotaa gamoo 4ffaa lakk. 408 argamtanii Xalayaa jijjirraa akka fudhattan isiin Beeksisna.

Hub

  •  sadarkaa Barnoota Dippiloomaafi Digrii akkasumas Gosa barnoota Afaan Oromoo fi Afaan Amaariffa alatti jijjirraan kun kan isin   hin ilaallanne ta’uu cimsinee isin beeksifna.
  • Jijjirraan kun Barsiisota Naannoolee irratti barsiisaa jiran qofa ilaallata.
  • yeroo xalayaa barreeffachuuf dhuftan gara xalayaan itti isiniif barraa’u  (Naannoo, godinaa,  Aanaa) murteeffattanii akka dhuftan gamanumaa isin hubachiifna.

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 13/6/2015 ዓ.ም

ማስታወቂያ!

በተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ቁጥጥር የስራ መደብ ለመወዳደር ከተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች ውስጥ ስማችሁ በዚህ የተጠቀሳችሁ ብቻ የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን ዋናውን እና ኮፒውን በመያዝ ከ14-16/6/2015 ዓ.ም በስራ ሰዓት በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በአካል በመምጣት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 13/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ፣ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተሞች እውቅና ሰጠ።

በእውቅና መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ተሸላሚ ተማሪዎች ፣ ወላጆች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ተማሪዎቹ እንዳስመዘገቡት ውጤት ላፕቶፖችን ጨምሮ ታብሌት ሞባይል እንዲሁም ለውጤቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት የምስክር ወረቀት ከክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዕውቅና መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ የተመዘገበው ውጤት አበረታች ቢሆንም ከከተማው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ በመጠቆም የግል ጥረታቸውን ተጠቅመው ውጤታማ የሆኑ ተሸላሚ ተማሪዎች በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በብቃት አልፈው ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ዜጋ እንደሚሆኑ እምነታቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የዛሬው የዕውቅና መርሀ ግብር በነበራቸው ያልተቋረጠ ጥረት ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎችን በማበረታታት ሌሎች ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን እና መንፈሳዊ ቅናትን ለመፍጠር እንደሚረዳ ጠቁመው ለውጤቱ መምጣት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ መምህራን ወላጆችና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በ2014ዓ.ም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 20 ፐርሰንት ያህል ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ትምህርት ቤቶች መካከል 10ሩ አዲስ አበባ እንደሚገኙ በመጥቀስ ውጤቱ በቀጣይ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለተሻለ ውጤት የምንተጋበት ይሆናል በማለት አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 10/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ በዋናነት በግል ትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚታዩ የትራፊክ መጨናነቆችን ለመቅረፍ በተዘጋጀ የመፍትሄ ኃሳብ ዙሪያ ከግል ትምህርት ቤት ባለሀብቶች ጋር የተካሄደ ሲሆን የግል ትምህርት ቤቶች እስከ 70 ተማሪ መያዝ የሚችሉ የተማሪ አውቶብሶችን እንዲጠቀሙና የከተማውን የትራንስፖርት አገልግሎት መጨናነቅ ማቃለል የሚያስችል የመወያያ ሀሳብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት በግል ትምህርት ቤቶች አከባቢ በተለይም በተማሪዎች መግቢያና መውጫ ሰዓት ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንደሚስተዋል ገልጸው በነዚህ ትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የተማሪ አውቶብሶችን መጠቀም ቢቻል ችግሩን ከመቅረፉ ባሻገር ተማሪዎች በሰዓቱ ትምህርት ቤት ደርሰው ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ የሚያስችል የመፍትሄ ሀሳብ በመሆኑ በቀጣይ ለተግባራዊነቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር  በጋራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አማረ በበኩላቸው ቢሮው ቀደም ሲል 94 የሚደርሱ መለስተኛ አውቶብሶችን ለግል ትምህርት ቤቶች አቅርቦ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸው አሁን የቀረበው አማራጭ ተማሪዎች ላይ የሚደርስ የትራፊክ አደጋን ከመቅረፉ ባሻገር የትራንስፖርት አገልግሎቱን ማዘመን የሚያስችል አሰራር በመሆኑ ቢሮው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የግል ትምህርት ቤቶችን ወደዚህ አገልግሎት የማስገባት ስራውን እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የቀረበው አማራጭ በትምህርት ቤቶቻቸው አከባቢ የሚስተዋሉ የትራፊክ ፍሰት ችግሮችን ከመቅረፉ ባሻገር የተማሪዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውምን አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 8/6/2015 ዓ.ም

#ማስታወቂያ!

አቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 8/6/2015 ዓ.ም

የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተናን ለማስተዳደር በተዘጋጀ አዲስ ሲስተም ዙሪያ ለክፍለ ከተማ የፈተና ዝግጅት ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡

ሲስተሙ ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ በተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅት የበለጸገ ሲሆን በሃገራችን ልጆች የተዘጋጀ እና ቀድሞ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍና መፍትሄ ለማምጣት የተሰራ እንደሆነና በቀላሉ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ሲስተም መሆኑን ገልጸው ወደፊት ከትምህርት ባለሞያዎች ጋር በመሆን  የተሻለ ስራ እንደምንሰራ አንጠራጠርም ሲሉ የድርጅቱ መስራች እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ምህንድስና መምህር የሆኑት አቶ ገብረመድህን መኮንን ተናግረዋል፡፡  አክለውም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ የሚወስዱ ተማሪዎችንም ሆነ ፈታኝ ትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ መረጃ የሚያስተዳድር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሲስተሙ ለአሰራር ምቹ ከመሆኑ ባሻገር በሀገር በቀል ድረጅት መዘጋጀቱ ከዚህ ቀደም ለውጪ ድርጅቶች ሲወጣ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ማስቀረቱን ገልጸው በ2015 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች ሲስተሙን በመጠቀም ከየካቲት 13 እስከ 17/2015 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን እንዲሁም ከየካቲት 20 እስከ 24/2015 ዓ.ም ድረስ ደግሞ የ6ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ኦን ላይን እንዲመዘግቡ ፕሮግራም መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ  አስረድተዋል፡፡