የሬዲዮ ትምህርት ይዘት መረጣ ግምገማ መካሄድ ጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ ኤፍ ኤም 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተተረጎመውን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እገዛ የሚያደርግ የሬዲዮ ትምህርት ዝግጅት የይዘት መረጣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ካከናወነ በሃላ ወደ ግምገማ ሂደት መግባቱን አሳውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት እና ትግበራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በለጠ ንጉሴ እንደታናገሩት በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተተረጎመውን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እገዛ የሚያደርግ የሬዲዮ ትምህርት ዝግጅት የይዘት መረጣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ሲካሄድ ቆይቶ መጠናቀቁን በመግለጽ ከዛሬ እለት ጀምሮ ወደ ግምገማ ምዕራፍ ገብቷል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ ኤፍ ኤም 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ ቡድን መሪ ወ/ሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸዉ የተከናወነው ይዘት መረጣ በአግባቡ ለመከናወኑ መገምገሙ እጅግ አስፈላጊ ሂደት መሆኑን በመጥቀስ ይዘት መረጣዉ ትክክለኛ ለመሆኑ፣ ተገቢ ይዘቶች በትክክል ስለመኖራቸዉ ፣ ሁሉም የትምህርት ምዕራፎች ስለመካተታቸዉ እና የይዘት መረጣዉ በቂ ስለመሆኑ ይፈተሻል ብለዋል፡፡ ግምገማዉ እደተጠናቀቀ በግምገማዉ የተገኙ ግብዓቶችን የማካተት ሰራ በቀጣይ ይከናወናልም ብለዋል፡፡
በግምገማዉ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ከአስራአንዱም ክፍለ ከተማ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት ላይ የተሳተፉ መምህራን፣ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያዎች ፣ የኤፌም 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች እና ከኦሮሚያ ክልል የመጡ የሬዲዮ ትምህርት አዘጋጆች መሆኑን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
