የኢንተርኔት ግንኙነት የሌላቸው ትምህርት ቤቶችን ሊጠቅም የሚችል ቴክኖሎጂ
ዲያስፖራው የኢንተርኔት ግንኙነት በሌለበት ቦታ የዲጂታል ትምህርት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለሙከራ ይዘው መጡ፡፡
ከ40 አመት በላይ አሜሪካን ሀገር የኖሩት አቶ ሚዴቅሳ በየነ የኢንተርኔት ግንኙነት በሌለበት ቦታ የዲጂታል ትምህርት መስጠት የሚያስችል መሳሪያ ለሙከራ ለሀገራቸው ይዘው መጥተዋል።
አቶ ሚደቅሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
በዚህም መሰረት ወደ ሀገር ሲመጡ የኢንተርኔት ግንኙነት የሌላቸው ትምህርት ቤቶችን ሊጠቅም የሚችል ቴክኖሎጂ ይዘው እንደመጡ ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው በሶላር ሃይል የሚሰራ፣ የራሱ ዋይፋይ ያለውና ተንቀሳቃሽ 2 ቴራባይት ሰርቨር የያዘ ሲሆን ከኮምፒውተርና ከሞባይል ጋር በማገናኘት የመማሪያ መሳሪያዎችን ማግኘት የሚቻልበት ነው።
ቴክኖሎጂው የተለያዩ የትምህርት አይነቶች የያዙ መፅሃፍት፣ መርጃ መፅሃፍት፣ ሌክቸሮችና ቪዲዮዎች፣ ጥናታዊ ፅሁፎች፣ ንግግሮች፣ መዝናኛዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎችንም ማስረጃዎች የሚይዝ ነው።
ከ60 ሺ በላይ መፀሃፍትን የያዘው ስርዓቱ መፅሃፍቶቹን በማንኛውም ጊዜ በነፃ ማውረድም ያስችላል።
በአሁን ሰዓት መሳሪያውን በሀገር ውስጥ ለመጠቀም እንዲቻል የትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ ባለሙያዎች እንዲገመግሙት እየተደረገ ነው።
ባለሙያዎቹ ሲስተሙ ላይ የሀገር ውስጥ የትምህርት አይነቶችን በመጫን ሀገርኛ ይዘት እንዲኖረው የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰሩም ተገልጿል።በቀጣይ የዚህን ቴክኖሎጂ ውጤታማነት ተገምግሞ ቀጣይ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።
ሌሎች ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ወደ ሀገር ሲመጡ የትምህርት ስርዓቱን ሊያግዝ የሚችል ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጠይቋል።
አካባቢያችንን #እንጠብቅ
ወደ ግንባር #እንዝመት
መከላከያን #እንደግፍ
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


