ቀን 18/9/2014 ዓ.ም

የተማሪዎች የማለዳ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በልደታ ክፍለ ከተማ

በልደታ ክፍለ ከተማ “በአካል ብቃት የተገነባ ጤናማ ዜጋ እንገነባለን” በሚል መሪ ቃል የተማሪዎች የማለዳ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተካሄደ።

በፕሮግራሙ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በክ/ከተማው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ ሎንቦሶ እንደተናገሩት የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ተማሪዎች የነቃ አዕምሮና ስነ-ልቦና በማዳበር ትምህርታቸውን በንቃት እንዲከታተሉ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

እንቅስቃሴው ጤናው የተጠበቀና በአካልና በአዕምሮ የተገነባ ትውልድ ከመፍጠር ባለፈ የተማሪዎችን የዕርስ በዕርስ ግንኙነትን በማጠናከር በተማሪዎች መካከል ቤተሰባዊነት እንዲጎለብት ያስችላል ሲሉ አቶ አሰፋ ገልፀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 16/9/2014 ዓ.ም

“ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 የትምህርት ዘመን በከተማዉ የሚሰጠዉ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ ወላጆች ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከምንጊዜውም በላይ የትምህርት ጥራት ፣ ተደራሽነት ፣ ተገቢነት እና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ የበኩላቸዉን ሚና በመወጣት ላይ በመሆናቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምስጋናዉን ያቀርባል፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ለትምህርታቸዉ ትኩረት ሰጥተዉ ከክፍል ክፍለ መዘዋወሪያ ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁበት ባለበት ወቅት ላይ ማህበራዊ ሀላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ ምህዳሮች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ እንዲሁም ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የሌለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እያሳወቀ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች “ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ” በሚል አሉባልታ ሳይጠለፉ እና ሳይምታቱ ለትምህርታቸው ትኩረት ስጥተዉ ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ እንድታደርጉ አደራ እንላለን፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 13/9/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙት ሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።

የጥያቄና መልስ ውድድሩ በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት እና በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ውድድሩ ቀደም ብሎ በሁለቱም ትምህርት ቤቶች በክፍል ደረጃ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚማሩ ተማሪዎች መካከል ተካሂዶ አሸናፊ የሆኑት በዛሬው የማጠቃለያ ውድድር ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል።

የጥያቄና መልስ ውድድሩ በተማሪዎች መካከል በጎ የፉክክር መንፈስን ከመፍጠሩ ባሻገር መምህራን በክፍል ውስጥ ያስተማሩትን ትምህርት ምን ያህል ተማሪዎች ተረድተውታል የሚለውን ለማወቅ እንደሚረዳም የአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ሱፐር ቫይዘር አቶ ይልማ ተሾመ አስታውቀዋል።

አቶ ይልማ አክለውም ሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ ደረጃ ሲመሰረቱ የልህቀት ማዕከል ሆነው ለሌሎች ትምህርት ቤቶች አርአያ እንዲሆኑ ታስቦ እንደመሆኑ በዚህ መልኩ የሚካሄድ የጥያቄና መልስ ውድድር ትምህርት ቤቶቹ  የተቋቋሙበትን አላማ ከግብ ለማድረስ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

በውድድሩ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ተማሪዎቹ ከፍተኛ ፉክክርና ትንቅንቅ ያዳረጉ ሲሆን አሸናፊዎቹም በየክፍል ደረጃው የሚከተሉት ናቸው።

ከ9ኛ ክፍል

1ኛ :- ተማሪ ዳዊት ፈይሳ ከገላን

2ኛ:- ተማሪ ዮሴፍ መኮንን ከገላን እንዲሁም

3ኛ:- ተማሪ ባይሴ ቱፋ ከእቴጌ መነን ሆነዋል።

ከ10ኛ ክፍል

1ኛ ፡- ተማሪ ኮከቤ አስቻለው ከእቴጌ መነን

2ኛ፡- ተማሪ ቢኒያም አባተ ከገላን

3ኛ፡- ተማሪ ቦንቱ ቡልቻ ከእቴጌ መነን በመሆን አሸንፈዋል።

ከ11ኛ ክፍል

1ኛ፡- ተማሪ አብረሀም ሀብቶም

2ኛ፡- ተማሪ ሀይረዲን መሀመድ

እንዲሁም 3ኛ ተማሪ ዮሀንስ ብርሀኑ በመሆን ሶስቱም ከገላን አሸናፊ ሆነዋል።

በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ደግሞ

1ኛ፡- ተማሪ ፍታሌ ታሪኩ

2ኛ፡- ተማሪ ቤተልሔም ታሪኩ

እንዲሁም 3ኛ ተማሪ ሰላማዊት አበባው ሶስቱም ከእቴጌ መነን አዳሪ ትምህርት ቤት ያሸነፉ ሲሆን በየክፍል ደረጃው አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 13/9/2014 ዓ.ም

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ አካሄደ።

በአውደ ርዕዩ ተማሪዎች በሳይንስና ሒሳብ ትምህርቶች ጨምሮ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በስዕል፣ ቅርጻ ቅርጽና በተለያዩ የስነ ጽሁፍ ስራዎች የሰሩዋቸው የፈጠራ ውጤቶች ቀርበው በተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተጎብኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ መክፈቻ የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ እባቡ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር ቀይረው በዚህ መልኩ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ማቅረባቸው ለሀገራችን እድገትና ሁለንተናዊ ብልጽግና የማይተካ ሚና ያለው ተግባር መሆኑን ጠቁመው የፈጠራ ስራዎች በዚህ መልኩ በተማሪዎችና መምህራን መዘጋጀታቸው አንዱ ከሌላው ልምድ ለመቅሰም እንደሚረዳውም አስገንዝበዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መስፍን ሀይሌ በበኩላቸው ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን የሰሩት የፈጠራ ስራ በቀጣይ ለሀገሪቱ ችግር መፍትሄ መስጠት የሚያስችል ተግባር በመሆኑ ከሚመለከተው አካል አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደርም ለትምህርት ሴክተሩ ተገቢውን እገዛ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።