የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ለማህበሩ አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀመረ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ከአደስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የአመራር ክህሎትና በራስ ስብዕና ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀምራል::
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠናው ለትምህርት ጥራትና ለተቋሙ ስኬት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል :: ስልጠናውም ተቋምን በመቀየር ሂደት የአመራሩ ሚና ምን መሆን እንዳለበት ግንዛቤ እንደሚሰጥ ገልፀዋል ::
ሰልጣኞች በስነባህሪ ግንባታ ራሳቸውን በመለወጥ ሌሎችን ማሰልጠን እንደሚጠበቅባቸው የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን ማህበር ትምህርት ስልጠናና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ወ/ሃና የተለወጠ የሰው ኃይል በማፍራት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን አስረድተዋል ::
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስልጠና 440 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ የመሰረታዊ መምህራን ማህበር ሰብሳቢዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማና የቴክኒክና ሙያ መዋቅር ሥር ያሉ የክፍለ ከተማ መምህራን ማህበር አመራሮች እንደሚሳተፉ ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/