ቀን 20 /1/2015 ዓ.ም

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት የምስጋና በዓል በመሆኑ በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን ለማጎልበት ያግዛል፡፡

ኢሬቻ በህዝብ መሰባሰብ አብሮነትን በሚያሳይ ደረጃ ደምቆ የሚከበር ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን የጨለማ ጊዜ አሳልፈኸን ብራን ልምላሜን ውበትን ያሳየኸን፤ ተፈጥሮን ሕይወትን መልሰህ  ያጎናፀፍከን፤ መሬቱን በልምላሜ፣ ድፍርሱን በጥራት የተካህልን፤ ወደ ብርሃንና መልካም ዘመን ያሻገርከን ፈጣሪያችን ምስጋና ይገባሃል በማለት ምስጋናውን የሚያቀርብበት እና ላጠፋነው ነገር ሁሉ ይቅር በለን እያለ ከፈጣሪው ጋር ጥልቅ ተፈጥሯዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት ታላቅ በዓል ነው።

ኢሬቻ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር የአንድነትን ፣ የብሮነትን እና የመተባበርን ስሜት የሚፈጥር ታላቅ በዓል በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ይህንን በሚያሳይ ደረጃ ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢሬቻ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሀብት በመሆኑ ሁሉም በእኔነት ስሜት በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የጋራ እና ከፍተኛ በሆነ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪዩን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

                   አመሰግናለሁ!

                 ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

                 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 18/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈተ ህይወት  የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛሉ፡፡

ፈጣሪ ነብሱን በአጸደ ገነት ያኑር!

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 16/1/2015 ዓ.ም

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !

መስቀል የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ የስኬት ማሳያ ሲሆን ደመራ የሁለንተናዊ አንድነታችን እና ጥንካሬያችን መገለጫ በመሆኑ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከብር በፍቅር በመረዳዳትና ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሚናችንን በመወጣት ሊሆን ይገባል፡፡

የዘንድሮ የመስቀልና የደመራ በዓል በ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት ልማት ስራችን ውጤታማ እንዲሆኑ በ2014 የትምህርት ዘመን በተከናወኑ አንኳር ተግባራት የተገኙ ዕመርታዊ የመማር ማስተማር ስራዎችን መለስ ብለን የተመለከትንበት እና በቀጣይ ስራዎቻችን ላይ ከመግባባት ላይ በደረስንበት በ29ኛዉ ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ማግስት የምናከብረው በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ላከናወናችዋቸዉ አመርቂ ስራዎች መስጋናዩን እያቀረብቁ የትምህርት ልማት ስራ በአንድ አካል ጥረት ብቻ ውጤታማ የሚሆን ባለመሆኑ በቀጣይ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚናችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እያልኩ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

                                                                ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

                                                የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 16/1/2015 ዓ.ም

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮማንድ ፖስት በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክፍለ ከተማ የትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች  ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ መጠን ፈተናዉ የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገቢዉን ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠዉ ኦረንቴሽንም በአግባቡ መከናወን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ለተፈታኞች የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ነገሮች ያቀረቡ ሲሆን በዚህም

የተፈታኞች መብቶች የሆኑት፡-  

  • ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት
  • በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት
  • ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት
  • የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት
  • በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት
  • ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት

የተፈታኞች ግዴታ የሆኑት፡-

  • ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ
  • ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት
  • ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ
  • ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም
  • ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት
  • ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ
  • ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት
  • ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት
  • ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት
  • ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ  ሲመጣ  አንሶላ፣  ብርድልብስና  የትራስ  ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት
  • ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት

ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች

  • አዲስ   ወይም  ቀድሞ  ለመማርና      ለማጥናት      ሲጠቀሙበት   የነበሩ   ማስተወሻ      ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
  • ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
  • ገንዘብ (ብር)
  • የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
  • የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች

  • ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
  • ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው
  • ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና  ሌሎች  ማንኛቸውም  ፎቶ፣  ምስል  እና  ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ  ዙሪያ  ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
  • በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት  ወይም  መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡
  • ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣  ሲጋራ፣  በሓኪም  ማዘዣ  የሌለው  መድኃኒት  (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
  • ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
  • ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
  • ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል  መግባት  እና  ፈተናው  ተጀምሮ  45 ደቂቃ     ሳይሞላ  ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
  • ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
  • በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
  • በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 15/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትላንትናው እለት ማካሄድ የጀመረውን 29ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ዛሬ አጠናቀቀ።

የትምህርት ጉባኤው  “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በጉባኤው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወተማን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የቀጣይ የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን ከጠቀሳቸው የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል በአንዳንድ ተማሪዎች እና በአንዳንድ መምህራን ላይ በሚታዩ የስነ ምግባር ችግሮችን መቅረፍ፣ ውስጣዊ እና ውጫዊ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ማስወገድ ፣ የተማሪዎች የምገባ አገልግሎትን ለማዘመን መስራት እንደሚገባ ፣ የትምህርት ተቋማት ደረጃቸዉን እንዳሻሽሉ እና የሚሰጡት ትምህርት የጥራት ደረጃዉን በጠበቀ ደረጃ እንዲሆን በትኩረት መሰራት፣ የመምህራንን ፣ የባለሙያዎችን እና የትምህርት አመራሮችን አቅም የማጎልበት ፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ አግዞ መስጠት ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት በመቀመር እና በማስፋት የትምህርት ተቋማት የመማማሪያ መድረኮች እንዲሆኑ ማድረግ እና የመረጃ አሰባሰብ ጥራትና ታማኒነትን ማዘመን የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በትምህርት ጉባኤው ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አብረውት በጋራ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የትስስር ፊርማ በቢሮው ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አማካኝነት የተፈራረመ ሲሆን በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በስራ አፈፃፀምና በተማሪዎች ውጤት የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ለወረዳና ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እውቅና ከመሰጠቱ ባሻገር በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።

ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር በትምህርት ሴክተሩ በ2014 ዓ.ም ከተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ የትምህርት ማህበረሰበቡ አካላት ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅባቸዋል ብለዋለ፡፡

በትምህርት ጉባኤው ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አብረውት በጋራ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶ ጋር የጋራ ስራ ፊርማ ከተከናወነ በሀላ የጉባኤው የአቋም መግለጫ ቀርቦ የመርሃ ግብሩ ፍጻሜ ሆናል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 14/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 29ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው በጠዋቱ ቆይታ ላይ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ ጌታውን ለማ በቢሮው እቅድ በጀት ዝግጅት እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና የ2014 ዓ/ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና ሪፖርት በአቶ ዲናኦል ጫላ በቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አማካኝነት ቀርባል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ እና የከተማ አስተዳደሩ ተወማ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌታቸው ሰጠኝ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኢንጂነር ጌታቸው ሰጠኝ በመልዕክታቸዉ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላቀ ደረጃ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወጡ እና የትምህርት ልማት ስራዉን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጎን የሚቆሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ማህበራቸው ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረባቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጣቸው ያሉ በመሆናቸዉ የከተማ አስተዳደሩን አመስግነው በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ጥያቄዎች የሚሰጣቸዉን ጥያቄዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በጉባኤዉ የከሰሀት ውሎም የቀረቡትን ሪፖርቶች መሰረት በማድረግ ውይይት በማናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በነገው እለትም በጋራ ለመሰራት ከተለያዩ ተቋማት ጋር የተስስር ሰነድ ፊርማ እና የተሸለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 14/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 29ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ጀመረ።

በጉባኤው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ዋነኛው አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ የተዘጋጀው የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ዝግጅት መሆኑን ገልጸው በዚህ ሂደትም ከትርጉም ጀምሮ እስከ መጽሀፍ ዝግጅት መምህራንን በማሳተፍ የተሰራው ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን ወጪ ቆጣቢ በሆነና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ማጠናቀቅ ማስቻሉን አስረድተዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ የትምህርት ግብዓት አቅርቦትን ጨምሮ  በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻል መታየቱንና በዋናነትም በ8ኛ ክፍል ፈተና 64.07% የሚሆኑ  ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመው የዘንድሮው የትምህርት ጉባኤ በርካታ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት እንደመሆኑ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚሆኑ ጠቃሚ ውይይቶች የሚነሱበት እንደሚሆን አስታውቀዋል።

የጉባኤው የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሪት ፋይዛ መሀመድ በበኩላቸው ትምህርት በዕውቀትና በስነምግባር የታነጹ ዜጎችን በማፍራት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ከተማሪዎች ምገባ ጀምሮ ዩኒፎርም፣ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ ምክር ቤቱም ለትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አገንዝበዋል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን የሚካሄድ ሲሆን የቢሮው የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 ዓ.ም እቅድ ፣የ2014ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና እንዲሁም የአዲሱ ስርአተ ትምህርት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር በአመቱ ለትምህርት ስራው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎች ዕውቅና እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 13/1/2015 ዓ.ም