ቀን 25/12/2014 ዓ.ም

የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ፅሁፍ ቀረጻ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ያዘጋጀው የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ቀረጻ ላይ እንደሚገኝና ቀረጻውም በቅርቡ ተጠናቆ  ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ከተዘጋጀው የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ለሬዲዮ መርሀ ትምህርት የሚሆን የይዘት መረጣ ተካሂዶ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች 900 ስክሪፕቶች ተዘጋጅተው በቀረጻ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ 

አቶ በለጠ አክለውም በአሁኑ ጊዜ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አንደኛ መንፈቅ አመት የሚያገለግሉ 450 የሚሆኑ ስክሪፕቶች ቀረጻ ላይ እንደሚገኙና በሂደቱም 75 የሬዲዮ ትምህርት ቀረጻ ፕሮግራም አዘጋጆችና ቴክኒሺያኖችን ጨምሮ  የተለያዩ ጭውውቶችንና መዝሙሮችን የሚጫወቱ ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸው ቀረጻው ሲጠናቀቅ የአርትኦት ስራ ተሰርቶ ለትምህርት አገልግሎት እንደሚበቃ አስረድተዋል፡፡  

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 24/12/2014 ዓ.ም

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋማት ቅድመ ዝግጅት በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን አስመልክቶ በዛሬው እለት በአንዶዴ ሁለተኛ ደረጃ ፣ በበሻሌ እና በጎሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋማት ቅድመ ዝግጅት ያሉበት ደረጃ ምን እንደሚመስል ምልከታ አድርጓል።

በዚህም ምልከታ ተማሪዎች ምዝገባ እያደሩ ለመሆኑ ለመመልከት የተቻለ ሲሆን በመጪው የትምህርት ዘመን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እየተሰሩ ለመሆኑ በበሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማየት ተችላል።

በቅድመ ዝግጅቱም ትምህርት ተቋማትን ለተማሪዎች ሳቢ እና ማራኪ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ለማድረግ ክፍሎችን  የማስዋብ ፣ አጥርና ግቢዎችን የማሳመር ፣ ለተማሪዎች ምቹ ያልሆኑ መቀመጫዎችን የመጠገን እና በተቋማቱ ዙሪያ ያሉ አዋኪ ተግባራትን ለማስወገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን ሲደረጉ እንደቆዩ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በምልከታውም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጥሩ ጅማሮ ላይ እንዳሉ ለመመልከት መቻሉን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩም ወርቁ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 21/12/2014 ዓ.ም

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በቀጣይ አመት ወደ ሙከራ ትግበራ እንደሚገባ ተገለፀ።

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ2015 ዓ.ም ይጀምራል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሙከራ ትግበራ ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን ስርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ዛፋ አብርሃ በበኩላቸው ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና  ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት ብዙ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ብለዋል።

በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል ።

የሚሰጠው ስልጠናም መምህራን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መጽሐፉ እዲተዋወቁ ይረዳቸዋል ተብሏል ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 20/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ላለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ውይይት አጠናቀቀ።

በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ  የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱዋቸው ሀሳቦች ለመድረክ ቀርበው ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በዋናነትም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፣ ለተማሪዎች የሚሰራጩ ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ቢሆኑ፣በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚገኙ አዋኪ ጉዳዮች በተማሪዎች ስነ ምግባር ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ስለሆነ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ችግሩን መቅረፍ ቢቻል፣በማስፋፊያ አከባቢዎች  ያሉ የመማሪያ ክፍል እጥረቶችን መፍታት ቢቻል፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል መስራት እንደሚገባ እንዲሁም የትምህርት አመራሩን ሙያዊ ብቃት ማሻሻል የሚያስችሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ቢሰጡ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተው በቢሮው ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰቷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ውይይቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ሀሳቦች የተነሱበትና የታለመለትን አላማ ያሳከ እንደነበረ ገልጸው ቢሮው በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት አስተባብሮ እንደሚሰራ አስታውቀዋል ።

ዶክተር ዘላለም አክለውም የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ የሚደረግበት ዓመት እንደመሆኑ ቢሮው ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ አሳትሞ በቅርብ ቀናት ለትምህርት ቤቶች ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በሙከራ ትግበራ የተገኘው ልምድ በሙሉ ትግበራው ወቅት ውጤታማ እንድንሆን አስተዋጾው ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በውይይቱ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ  በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈቤት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ መምህራን ማህበር ፣ ከወላጅ ተማሪ ማህበር እንዲሁም ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ጋር በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በጋራ መስራት የሚያስችለውን የፊርማ ስነ ስርአት አካሂዷል ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 20/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሶስት ቀን ቆይታ ሲያካሂደው የቆየው ግምገማ እና ውይይት የማጠቃለያ መርሃ ግብር መካሄድ ጀምራል።

በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆኑ ተሳታፊዎች ለግምገማዉ እና ውይይቱ በተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን ሰፊ ውይይት በማድረግ የማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ ጀምረዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ማርቺንግ ባንድ ጥሁመ ዜማዎችን በማቅብ ለመድረኩ ድምቀት ከመሆኑም ባሻገር የኢትዩጵያን ብሄራዊ ህዝብ መዝሙርን በማቀረብ መርሀ ግብሩን ለማስጀመር ችለዋል፡፡

ደራሲ ገጣሚ እና ተመራማሪ አበራ ለማ ተገኝተዉ የብዕር ቱሩፋታቸዉን ለመድረኩ አቅርበዋል፡፡

በግምገማ እና ውይይት መርሃ ግብሩም የጋራ የፊርማ መርሃ ግብር የሚከናወን መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችላል፡፡  

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 18/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሶስት ቀን የሚቆይ ውይይት ማካሄድ ጀምራል።

በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆኑ ተሳታፊዎች ለግምገማዉ እና ውይይቱ በተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን ሰፊ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ግምገማዉ እና ውይይቱ እስከ አርብ ድረስ ቆይታ በማድረግ የሚጠቃለል ይሆናል፡፡   

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 18/12/2014 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ደረጃ ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ  ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም  መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ መስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 18/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሶስት ቀን የሚቆይ ውይይት ማካሄድ ጀመረ።

በመርሀ ግብሩ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገ ኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን  ተሳታፊዎች ለመውያያነት በተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን ሰፊ ውይይት እንደሚካሂዱ የወጣው መርሀ ግብር ያሳያል።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ በ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን አበረታች ውጤት መመዝገቡን እና እንደማሳያም በስምንተኛ ክፍል 63% የሚሆኑ ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸው በዘርፉ ለተገኘው የላቀ ውጤት በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች አስተዋጾ ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋና እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በተማሪዎቻችን ውጤት መሻሻል ላይ እየተመዘገበ የሚገኘውን አበረታች ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው በየትምህርት ተቋማቱ አከባቢ የሚገኙና በተማሪዎች ስነምግባር ላይ ችግር የሚፈጥሩ አዋኪ ጉዳዮችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸው በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግና ለዚህም አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው በትምህርት ሴክተሩ ከቅድመ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው በውይይቱ በአፈጻጸም የታዩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችሉ ኃሳቦችን በማንሳት በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 17/12/2014 ዓ.ም

በፍሬህይወት ቁጥር 2 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ተቋሙን ምድረ ግቢ ምቹ የማድረግ ስራ ተከናወነ፡፡

በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፍሬህይወት ቁጥር 2 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ምድረ ግቢ ለመማር ማስተማር ስራዉ ምቹ የማድረግ ስራ ተከናወነ፡፡

በክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ጽ/ቤት እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ተማሪ ወላጆች ህብረት አሰተባባሪነት ምድረ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ የኮብል እስቶን ንጣፍ ተሰርቶ በዛሬዉ እለት ተመርቋል፡፡

የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ እና የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ የሆኑት አቶ መለስ ጋሻው በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት እና በመመረቅ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን አድርገዋል፡፡