እንኳን ደስ አላችሁ! የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆናል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆናል፡፡
ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን የተሻለ ውጤትም የተመዘገበ በመሆኑ ተማሪዎች ፣ ወላጆች በአጠቃላይ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡
የፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬዉ እለት የተሰራጨ ሲሆን ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ውጤታችሁን በየትምህርት ቤቶቻችሁ መመልከት እንደምትችሉ ይጠበቃል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
