ቀን 7/12/2014 ዓ.ም

የቦሌ ክፍለከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ308 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 47 ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

አሰሰተዳደሩ  በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 22 የ60 ቀናት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ  የትምህርት ፣ የጤና ፣ የስፖርት እና ሌሎችም ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፕሮጀክቶችን እንዳጠናቀቀ የክ/ከተማው የዲዛይንና ግንባታ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር አባይነህ ባጫ ገልፀዋል፡፡

በጊዜ ማዕቀፉ ፅ/ቤቱ ግንባታቸውን አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ካደረጋቸው ፕሮጀክቶች መካከል

  • መገኛው ወረዳ 13 የሆነውና  ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወሰደው የቦሌ ሕብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት G+4 ህንፃ፤
  • የውለታ መጠኑ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነው የወረዳ 10 መሪ ትምህርት ቤት 3*1 ሜዳ፤
  • በወረዳ 09 ውስጥ በብቸኝነት የሚገኘውና 30 ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጎ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ  የተገነባው የምስራቅ በር ቁጥር 2 አፀደ ሕፃናት፤
  • 13 ሚሊዮን ብር የወጣበት ወረዳ 09 ጎሮ G +2 ቤተ-መፅሐፍት ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሌሎችም ሰፊ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ፕሮጀክቶች በፅ/ቤቱ ባለቤትነት ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 6/12/2014 ዓ.ም

“ የአፍሪካ የጥቁር መሬት ወንዞች አባት የማይደክመው የማይታክት ብርቱ ፤ የኛው አባይ የጀግንነት የእምቢታ ምስክር ነው፡፡

ባደገበት ባይተዋሩ የተባለለት አባይ ዛሬ መጎማሸሩን ቀጥሎ ለሀገሩ ልጆች ኩራትና ብርሃን መሆን ችላል፡፡

ውድ ኢትዮጵያዊያን የሕዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ እና የጀመርነውን የምንጨርስ መሆኑን ያሳየንበት ሌላኛው የከፍታ ክዋኔ ላይ በመድረሳችን እንኳን ደስ አለን! አላችሁ!፡፡ ”

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 6/12/2014 ዓ.ም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር ሙሌት ፎቶዎች

እንኳን ደስ አለን!

የሕዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

የክረምት ወቅት መግባትን ተከትሎ ለሶስተኛ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የግድቡ የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ስራዎች ግንባታ 95 በመቶ የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸምም 83 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ስራ በትናንትናው ዕለት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በትናንትናው ዕለት ስራ የጀመረው ዩኒት ዘጠኝ ሲሆን  ባለፈው የካቲት ወር ዩኒት10 ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የሚታወቅ ነው።  

ግድቡ አሁን ባለው ከፍታና በያዘው የውሃ መጠን ሁለቱ ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት ሃይል እያመነጩ ይገኛሉ።

ግድቡ በሙሉ አቅሙ ሃይል ማመንጨት ሲጀምር ደግሞ እያንዳንዱ ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ሃይል የሚያመነጭ ይሆናል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ዋናው ግድብ ከፍታ 145 ሜትር ሲሆን፥ ርዝመቱ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ነው።

ግድቡ 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ስፋት የሚሸፍን ሲሆን፥ 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር የውሃ መጠን ይይዛል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 5 /12/2014 ዓ.ም

እንኳን ደስ አለን!

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ፡፡

በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ  የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሁለተኛ ተርባይኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው  እውን ሆኗል።

ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 4/12/2014 ዓ.ም

ማስታወቂያ!/ BEEKSISA!

ማስታወቂያ!

ቀን 2/12/2014 ዓ.ም

ዛሬ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በ60 ቀናት ተገንብተው የተጠናቀቁና ነባር የተለያዩ 57 ፕሮጀክቶች ተመረቁ ::

አድዋ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፥ የምገባ ማዕከል : የተለያዩ ፓርኮች ፥  የክፍለ ከተማ የአስተዳደር ህንፃ ፧የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ፥ 7 ፖሊስ ጣቢያዎች ፥  የአደባባይ ማስዋብ ፕሮጀክቶች፥ የዳቦ ፋብሪካና መሸጫ ሱቆች ዛሬ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች  ውስጥ ናቸው::

በፕሮግራሙ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የምንመርቀውን ጨምሮ በ2014 ዓ.ም ይዘናቸው የነበሩ 334 ፕሮጀክቶች በስኬት ማጠናቀቅ ችለናል ያሉ ሲሆን እነዚህ ብቻ ሳይሆን ደግሞ በህዝባችን ፤ በበጎ አድራጊ ባለሃብቶች  ትብብር ደግሞ ሌሎች ከ300 በላይ ፕሮጀክቶች መሰራት ችለዋል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ከንቲባ አዳነች  ፕሮጀክቶችን በመገንባት ሂደት  ፤ህዝቡ  ከጎደሎው  እያወጣ በየአካባቢው ተሳትፎው የማድረጉ ባህል  እየተጠናከረ መምጣቱ በእጅጉ የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡

ከዝህ ቀደም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል እሳቤ ብዙ ፕሮጀክቶች ተጀምረው ጥለው የተሄዱና የህዝብ ሃብት በማባከን ብዙ ጉዳት ደርሰዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች   ነገር ግን እነኚህን በየአካባቢው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለቅመን የህዝብ ሃብት ስለሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተን በመስራት አጠናቀን ለህዝብ ጥቅም አውለናል ብለዋል፡፡

አሁንም ከለውጥ በፊት የተጀመሩ ውላቸውን ለማቋረጥ እንኳን ያላገኘናቸው ኮንትራክተሮች አሉ ያሉት ከንቲባዋ፤ ሃገር የምትገነባው በጋራ ነው ፥ ፕሮጀክቶች ስንጨርስም  የምንጠቀምበት በጋራ ነው።

ባለሃብቶች የሚያድጉትም የሚለወጡት ህዝብ በተገቢው አገልግሎት ሲያገኝ ነው ሲሉም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ትርጉማቸው ብዙ ነው በክ/ከተማው ተቋማት በተለያየ ቦታ ቢሮ ኪራይ ሲከፍሉ የነበረበት እና ህዝቡ ሲጉላላ የነበረበት ነው፡፡

ስለሆነም ህዝቡን አክብረን ልናገለግልበት ፤ ለህዝብ የገባነውን ቃል ልንተገብርበት ነው፤ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ልትሰጡበት ይገባልም ብለዋል።

ለዚህ ፕሮጀክት ስኬት ፕሮጀክቱ በተጓተተበት ጊዜ በመድረስ   የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎችን የጎደለውን በመሙላት  ላደረገው አስተዋፅኦ እናመሰግናለንም በማለት ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 1/12/2014 ዓ.ም

የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ሁኔታ ላይ ቁጥጥር እንደሚካሄድ ባለሥልጣኑ ገለጸ፡፡

የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ ሲያጠናቅቁ የቁጥጥር ሥራ በማካሄድ ከመመሪያ ውጪ ያልተገባ ክፍያ አስከፍለው የተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ።

አላግባብ የክፍያ ጭማሪን አስመልክቶ ከወላጆች የቀረቡ ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ ሲያጠናቅቁ ባለስልጣኑ ቁጥጥር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቁመዋል።

‹‹የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ ሲያጠናቅቁ ቁጥጥር ይካሄዳል፣ በመመሪያው መሠረት ያላግባብ ያስከፈሉ ካሉ ገንዘብ እንዲመልሱ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ አስተዳደራዊ ርምጃዎች ይወሰዳል›› ነው ያሉት።

በተደረገው አጭር ምልከታ 12 የግል ትምህርት ቤቶች ጭማሪን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ ጥሰው በመገኘታቸው ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጅ መልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉ መታዘዙንም ተናግረዋል።

በመመሪያ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱ ናቸው ያሉት ኃላፊዋ፤ አንዳንድ ተቋማት የምዝገባ ክፍያ መጨመር፣ በዓይነት መጠየቅ እና የመሳሰሉ ያልተፈቀደ ክፍያ ጭማሪ እያደረጉ እንደሚገኙ ጥቆማ ደርሶናል፤ ወርደን እያስተካከልን እንገኛለን ብለዋል።

ለክትትል የሚላኩ ባለሙያዎች አቅጣጫ ተሰጥቶአቸዉ እንደሚላኩ በመጠቆምም፤ ባለሙያዎች የተከፈለበትን ደረሰኝ ተመልክተው እንዲያረጋግጡ የሚያደርግ የመገምገሚያ ሰነድ ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።

ተግባሩ ባለሀብቶቹን ማነጋገር ብቻ አይደለም፣ ደረሰኝ ተመልክተው እንዲያረጋግጡ፣ ከተቻለም በየአንዳንዱ ተቋም የተወሰኑ ወላጆችን ማነጋገር የሚቻልበት አሠራር ተዘርግቷል ብለዋል፡፡

ከባለሙያዎች አቅም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተቋማትን ለማየት በቅርንጫፍና በዋና መስሪያ ቤት ያሉ ባለሙያዎች በማሰማራት በሚገባ ለመገምገም ዝግጅት ተደርጓል። ከመመሪያው ውጪ ወርሃዊ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ ማድረግና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን አስከፍለው በተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ ይወሰዳል፣ ለሕዝብም ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

በአብዛኛው እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ምዝገባ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ከነሐሴ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማትን በመዘዋወር የሚደረገው ምልከታ ያላግባብ ክፍያ የተቀበሉ የትምህርት ተቋማት ገንዘብ እንዲመልሱ ከማድረግ ጀምሮ አስተዳደራዊ ርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

‹‹ከመደበኛ ክፍያ ውጪ በየትኛውም መልኩ ክፍያ ማስከፈል አይቻልም፣ አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ፤ መጽሐፍም ሆነ ደብተር መሸጥ አይችልም። ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ የተንቀሳቀሰ ተቋም ከተገኘ ርምጃ ይወሰድበታል›› ብለዋል።

መመሪያው በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት ጭማሪ እንዳያደርጉ እንደሚያዝ አስታውሰዋል።

አምና ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ መጨመር እንደማይችሉ ለመቆጣጠር የማስፈጸሚያ መመሪያ ተዘጋጅቷል። ዓላማው የኅብረተሰቡ የመክፈል አቅም፣ የኑሮ ውድነት ችግርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አምና የጨመሩ ተቋማት እንዳይጨምሩ ለማድረግ ነው ሲሉም መናገራቸዉን ኢ ፕ ድ ዘግባል ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

ቀን 1/12/2014 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ከአለም 3ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ የተካሄደውን የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም 12 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በውድድሩ ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳሊያ ከአፍሪካ በአንደኝነት አጠናቃለች።

ይህም ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪክ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው ሲሆን በውድድር ተግባራት አንፃር ሲታይ እጅግ የሚያኮራ ውጤት መመዝገቡ ተገልጸዋል።