የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮጀክት የቦርድ አባላት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመስክ ምልከታ አካሄዱ።
የመስክ ምልከታው አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኙት ዳግማዊ ሚኒሊክ እና ገነት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን በጉብኝቱ የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮጀክት የቦርድ ሰብሳቢ ጄሚ ኩፐር፣የፕሮጀክቱ አባልና የቀድሞው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ፣የከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ጥላሁን ወርቁን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በዋናነት በትምህርት ቤቶቹ ያለውን የትምህርት አሰጣጥ እንዲሁም የተማሪዎችን የማሸለቢያና የመመገቢያ ክፍሎች ከማየታቸው ባሻገር ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተመልክተዋል።
በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ9 የስልጠና ጣቢያዎች ለሁለተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰቷል።
ስልጠናው ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የተዘጋጀ የማሰልጠኛ ማኑዋልን መሰረት አድርጎ ለ1,500 የአማርኛና አፋን ኦሮሞ መምህራን መሰጠቱን በትምህርት ቢሮ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ወይዘሪት ትግስት ድንቁ ገልጸው ቀደም ሲል ለ1,102 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/