ቀን 21/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሚገኘው ኤፍ ኤም 94.7 የሬዲዮ ጣቢያ ጉብኝት አካሄደ።

በጉብኝቱ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሚኒ ሚዲያ ክበብ ተጠሪዎችና አባላትን ጨምሮ የሬዲዮ ትምህርት ተጠሪዎች እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮችና የክፍለ ከተማ የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ጉብኝቱ በዋናነት የሚኒሚዲያ ክበባቱ አባል ተማሪዎቹም ሆኑ ተጠሪ መምህራኑ በሬዲዮ ጣቢያው ያለውን አሰራርም ሆነ የስቱዲዮ አደረጃጀት በመመልከት በየትምህርት ቤቶቻቸው በተሻለ ሁኔታ ክበባቱን እንዲያደራጁ ታስቦ መካሄዱን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ቤኩማ ደበሎ ገልጸው የሚኒ ሚዲያ አባል የሆኑት ተማሪዎች መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ዕውቀት እንዲኖራቸው ጉብኝቱ አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም በሬዲዮ ጣቢያው   የተመለከቱት የስቱዲዮ አደረጃጀትም ሆነ አሰራር በየትምህርት ቤቶቻቸው ከበባቱ በተሻለ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ ከማስቻሉ ባሻገር ወደፊት በጋዜጠኝነትና ተያያዥ ሙያዎች መስራት ለሚፈልጉ ተማሪዎች ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 21/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አለም አቀፉን የጸረ ሙስና ቀን በማስመልከት ሙስናን መታገል በተግባር በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስራት ሽፈራው ከፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የወረደን ሰነድ  ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር ያቀረቡ ሲሆን የትምህርት ሴክተሩ ሙስናንም ሆነ ብልሹ አሰራርን ለመታገል በየትምህርት ቤቶቹ የተደራጁ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና  ክበባትን ከማጠናከር ጀምሮ ለተማሪዎች የግብረ ገብነትን ትምህርት በአግባቡ ማስተማር እንደሚገባ አስረድተዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ሙስና የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል በሰጠው ከፍተ ኛ ትኩረት ብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የትምህርት ማህበረሰቡም ሙስናንም ሆነ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ ከችግሩ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ የአስተሳሰብ ዝንፈቶችን በማስተካከል ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው ከሀገራዊ ለውጡ ከሙስናም ሆነ ብልሹ አሰራር በተገናኘ ለሚካሄደው ትግል ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ጠቁመው ችግሩን ለመከላከል ተቋማዊ አሰራርና አደረጃጀትን በማጠናከር ደንብና መመሪያን ተከትሎ መስራት እንደሚገባ አስታውቀዋል።   

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 20/3/2015 ዓ.ም

ሌብነትን/ሙስናን/ ሀገራዊ የህልውና አደጋ አድርገን ልንታገለው ይገባል፡- የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከትምህርት ማህበረሰቡ አባላት ጋር “ሌብነትን መታገል በተግባር” መሪ ሃሳብ ሙስናን መታገል በሚቻልበት ጉዳይ ከመምህራን፣ ከተማሪዎችና ከወተመህ አባላት ጋር የተሳካ የንቅናቄ መድረክ መካሄዱን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ አስታውቀዋል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ ሌብነት/ሙስና/ ሃገር እድገትን የሚያቀጭጭ  የእድገት ፀር በመሆኑ ሁላችንም በተባበረ ክንድ ልንታገለው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱልሰመድ ሻሚል በበኩላቸው ሌብነትን/ሙስናን/ ሃገራዊ የህልውና አደጋ አድርገን ልንታገለው የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ የት/ት ዘርፉ ባለሙያዎችም የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው መግለጻቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው ወረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 19/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ሲያካሂድ የነበረውን የፓናል ውይይት በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡

ውይይቱ ዛሬ በቢሮ ደረጃ ሲጠቃለል በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር አመራሮችእና የወላጅ ማህበር ተወካዮች መምህራን እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ዜጋና ስነምግባር ስርአተ ትምህርት ባለሙያው አቶ ዘሪሁን አለማየሁ በፌደራሊዝም ስርአት ጽንሰ ሀሳብ ምንነትና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ  ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ተመሳሳይ ውይይት ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸው በውይይቶቹም በዋናነት በሀገራዊም ሆነ ህገመንግስታዊ ጉዳዮች የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሀሳቦች መነሳታቸውን አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ዘላለም አክለውም ኢትዮጵያ ከወሰነቻቸውና በታሪክ ከሚነሱ ውሳኔዎች መካከል አንዱ የፌደራል ስርአቱን ተግባራዊ ያደረገችበት አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመው የትምህርት ማህበረሰቡ በህገመንግስቱም ሆነ የፌደራል ስርአቱ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ ጨብጦ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ የፌደራል ስርአቱ የህዝቦችን እኩልነትና እራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያከበረ በመሆኑ ከጽንሰ ሀሳቡ ጋር በተገናነ የሚታዩ የተዛቡ አስተሳሰቦችን በማረም ብዝሀነትን ያከበረ ስርአት መፍጠር እንደሚገባ ሲገልጹ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው የጋራ የሆነችውን ሀገራችንን በሚፈለገው ደረጃ ለመገንባት ህብረብሄራዊ አንድነታችንን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 17/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል ሲያካሂድ የቆየውን የጥያቄና መልስ ውድድር በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡

የጥያቄና መልስ ውድድሩ ቀደም ብሎ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ህገመንግስቱንና የፌደራል ስርአቱን መሰረት በማድረግ በቀረቡ ጥያቄዎች ተወዳድረው አሸናፊ ሆነው በቀረቡ 5 የአማርኛና 5 የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን በአሸናፊዎች አሸናፊ የማጠቃለያ ውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር፤ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሪት ፋይዛ መሀመድ፤የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፤በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩርን ፤ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች፤ወላጆች ፤መምህራን እና ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ተካሂዱዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር በጥያቄና መልስ ውድድሩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ዘንድሮ በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ  ብሄሮች ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በትምህርት ሴክተሩ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሲከበር ቆይቶ በዚህ መልኩ በተማሪዎች መካከል በሚካሄድ የጥያቄና መልስ ውድድር መጠናቀቁ የትምህርት ሴክተሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚፈሩበት እንደመሆኑ ትውልዱ ህገመንግስቱንም ሆነ የፌደራል ስርአቱን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ኖሮት ጸረ ሰላም የሆኑና ለሀገር አንድነት እንቅፋት የሆኑ አስተሳሰቦችን መታገል እንዲችል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የኢትዮጵያ  ብሄሮች ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበሩ በህገመንግስትና ህገመንግስታዊ  ስርአቱ ዙሪያ ህብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ  እንዲያገኝ ከማስቻሉ በላይ በህዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ የመኖር ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ምቹ  ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸው  የትምህርት ሴክተሩም ቀኑን በማስመልከት ከትምርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው በተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር፤ በፓናል ውይይቶችና በተለያዩ ፌስቲቫሎች ሲያከበር መቆየቱን በመጥቀስ በአሉ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው በድምቀት እንዲከበር ላስቻሉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአሸናፊዎች አሸናፊ የማጠቃለያ ጥያቄና መልስ ውድድሩ በአማርኛው ስርዓተ ትምህርት 1ኛ ተማሪ ነጂብ አማን ከአዲስ ከተማ ፤ 2ኛ ተማሪ ፍቅር በሱፍቃድ ከአቃቂ ቃሊቲ ፤እንዲሁም 3ኛ ተማሪ እያሱ በቀለ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ አሸናፊ ሲሆኑ በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ደግሞ 1ኛ ተማሪ ጨራ ሀብታሙ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ 2ኛ ተማሪ አጸደ ተካ ከቦሌ እንዲሁም ተማሪ ቤተሊሄም አዲሱ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነው የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 14/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ “ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ፡፡

የጥያቄና መልስ ውድድሩ ቀደም ብሎ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ክፍለከተማ ድረስ ተካሂዶ አሸናፊ ሆነው በቀረቡ ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን በውድድሩም ከአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ 22 የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ታለማ በጥያቄና መልስ ውድድሩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ህገ መንግስቱን እና ፌደራሊዝም ስርአቱን መሰረት ባደረጉ ጥያቄዎች እንደሚካሄድ ገልጸው በዛሬው ውድድር አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችም በመጪው ቅዳሜ በድምቀት በሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ወድድር ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ በበኩላቸው በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው ውድድሩ ተማሪዎቻችን በትምህርት ስርአቱ ህገመንግስቱንም ሆነ የፌደራል ስርአቱን መሰረት በማድረግ የሚሰጠውን ትምህርት በአግባቡ መረዳታቸውን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ  ገልጸዋል፡፡

በጥያቄና መልስ ውድድሩ በአማርኛው ስርዓተ ትምህርት አራዳ፤ልደታ፤አዲስ ከተማ፤ኮልፌ ቀራንዮ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች አሸናፊ ሆነው ለፍጻሜ ማለፋቸውን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያው አቶ ዘሪሁን አለማየሁ ሲገልጹ በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ደግሞ አራዳ፤ኮልፌቀራንዮ፤አቃቂ ቃሊቲ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለከተሞች አሸናፊ በመሆን በመጪው ቅዳሜ ለሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 14/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት 17ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የባህል ሲምፖዚየም አካሄደ፡፡

‹‹ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን›› በሚል መሪ ቃል የ2015 ዓ.ም 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ስናከብር ያሉን ባህላዊ እሴቶች አንድነታችንን የሚያጠናክሩና የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ ስለሆኑ ልንጠብቃቸውና ለሌሎች ልናጋራቸው ይገባል ሲሉ የክፍለ ከተማው ትምህርተ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልፀዋል፡፡

በፊሊጶስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በተካሄደው የባህል ሲንፖዚየም በ1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተዘጋጁ የብሄር ብሄረሰብ አልባሳት፣ ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ ውዝዋዜዎች እና ባህላዊ መጠቀሚያ እቃዎች በማሳየት በተደረገው የባህል ሲምፖዚየም ላይ ውድድር በማካሄድ ስራቸውን ላቀረቡ ት/ቤቶች በሙሉ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ት/ቤቶች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት በመስጠት በደማቅ ሁኔታ መካሄዱን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ት/ቤቶች የሚከተሉት ናቸው፡-  

  1. ፊሊጶስ ቅድመ አንደኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፡- 93.9 ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ
  • አበቦች ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፡-  93.1ውጤት በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃ
  • ጉለሌ ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፡- 88.1 ውጤት በማስመዝገብ 3ኛ ደረጃ ተብለው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 13/3/2015 ዓ.ም

ማስታወቂያ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ13/02/2015 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው የስራ ቅጥር ማስታወቂያ በ IT (Information Technology) እና በPVA (performing and vissual art) ተወዳድራችሁ ፤ ፈተና ወሰዳችሁ ያለፋችሁ እና ስማችሁ የተጠቀሰ አመልካቾች በቀን 15/03/2015 ዓ.ም በተመደባችሁበት ክፍለ ከተማ በመሄድ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

 ማሳሰቢያ ፡ በተጠባባቂ ላይ ስማችሁ የተዘረዘረ እንዳስፈላጊነቱ በስልክና በቴሌግራም የምንጠራችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  BEEKSISA!

Biiroon Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee Barsiisotaa Gosa Barnootaa IT Digirii fi PVA (Performing Vesual Arti)tiin Dippiloomaa fi Digiriidhaan dorgomsiisee Qacarrii gaggeessuuf Gaafa Guyyaa 13/02/2015A.L.I Gaazexaa Aaddis zaman irratti beeksisa baasuun galmeen on-line irratti gaggeeffamaa turuun isaa ni yaadatama.

Haaluma kanaan Dorgomtoonni Qormaata fudhattanii, Qormaata dabartanii maqaan keessan gara Fuula weebsaayitii kanaa irratti gadi lakkifamtan gaafa Guyyaa 15/03/2015 A.L.I tti kutaa Magaalaa irratti ramadamtanitti argamtanii gabaasa akka gootan gamanumaa isin beeksifna.

Hubachiisa:-

Dorgomtoonni maqaan keessan eeggattoota irratti gadi lakkifamtan gara fuula weebsaayitii fi Telegraama Biiroo Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfenneetiin akka hordoftan isin beeksifna.

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 9/3/2015 ዓ.ም

በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን “ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላም “በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አከበረ።

በበዓሉ ላይ የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በመገኘት ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት 17ተኛው የብሔር ብሔረሰቦችን ቀንን ስናከብር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የምናከብር ሲሆን በዝግጅቱ ላይም ፌስቲቫል የተለያዩ ትዕይንቶችና እንዲሁም የፓናል ውይይት የተማሪዎች ህገ መንግስትን መሠረት ያደረገ ጥያቄ እና መልስ ውድድር የተደረጉ ሲሆን ይህም እስከ ህዳር 29 ይቀጥላል ብለዋል።

ብሔር ብሔረሰብ ቀንን ስናከብር አንድነታችንን እና እሴታችንን ሊያጠናክር የሚችል ሀገረ መንግስት የምናጎለበትበት ሲሆን ሀገራችን ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች በወንድማማችነት እና በህትማማችነት የሚኖሩባት የነዚህን ባህል ቱፊት ማጠናከር መቻል በሚያስችል አግባብ መሆን አለበት በማለት ገልፀዋል።

በመቀጠልም የምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባዔ ወ/ሮ ሰርካለም አበበ ብሔር ብሔረሰብን ስናከብር በባለፈው ስርዓት የሚነሱ የባህል የቋንቋ የሀይማኖት ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ህዳር 29/1987 የፀደቀ ሲሆን በ1998 ጀምሮ በአገራችን ለ17ተኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በት/ጽ/ቤት የስራዓተ ትምህርት ቡድን መሪ የሆኑ አቶ ገዳ ሞሲሳ የብሔር ብሔረሰብ ቀን በትምህርት ተቋም ስናከብር ትልቅ ቦታ በመስጠት በዓሉ የሚከበር ሲሆን ልዩነታችን ውበታችን መሆኑን አውቀን በደመቀ መልኩ እናከብራለን ብለዋል።

በመጨረሻም ለፓናል ውይይቱ የሚሆን ሰነድ ከመድረክ በዝርዝር ቀርቦ በቀረበው ሰነድ ላይ የተለያዩ አስተያየት ሀሳብ እና ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በቀረቡት ላይ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ እና የምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሰርካለም አበበ ማጠቃለያ ሀሳብ መስጠታቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ቀን 8/3/2015 ዓ.ም

ማስታወቂያ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ13/01/2015 ዓ ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ  በወጣው የስራ ቅጥር ማሰታወቂያ መሰረት በቢሮ ድህረ ገጽ (online) ላይ  IT (information technology ) ድግሪ ለመቀጠር  ተመዘገባችሁ የመጀመሪያ  እና የለሁለተኛ ማጣሪያ  በማለፍ ስም ዝርዝራችሁ በትምህርት ቢሮው telegeram ,facebook፣twitter፣instageram እና ድረገጽ አድራሻዎች  ላይ  የተጠቀሳችሁ ተወዳዳሪዎች  ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ  በመያዝ  በ10/03/2015 ዓ.ም  ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በዳግማዊ ሚኒሊክ ከፍተኛ 2ኛ ደረጀ ትምህርት  ቤት በአካል ተገኝታችሁ  እንድትፈተኑ  እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ!

ከተገለጸው ስም  ዝርዝር ዉጭ ማንንም  የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

Biiroon Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee Barsiisotaa Gosa Barnootaa IT (information technology) Digiriidhaan dorgomsiisee Qacarrii gaggeessuuf Gaafa Guyyaa 13/02/2015 A.L.I Gaazexaa Aaddis zaman irratti beeksisa baasuun galmeen on-line irratti gaggeeffamaa turuun isaa ni yaadatama.

Haaluma kanaan Dorgomtoonni calallii duraatii fi lammaffaa dabartanii maqaan keessan gara fuula telegeram, facebook፣ twitter፣ instageram fi weebsaayitii Biiroon Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinneerratti gadi lakkifamtan gaafa Guyyaa 10/03/2005 A.L.I ganama keessaa sa’aatii 2:30 irratti Waraqaa eenyumaa keessan ibsu qabattanii Mana Baruumsa Minilik sad.2ffaa tti argamuun qormaata akka fudhattan gamanumaa isin beeksifna.

Hubachiisa:-

1. Warreen maqaan keessan as irratti hin ibsamin dhufuun isin hin barbaachisu

2. Dorgomtoonni Guyyaa caqafame dabarsitanii dhuftan kan isin hin keessummeessine ta’uu gamanumaa isin hubachiifna

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/