አራብሳ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አገልግሎት ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ትምህርት ቤቱ ተግባራዊ ካደረጋቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር 9715 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ማስተላለፊያ መስመርን በመጠቀም ከተማሪ ወላጆች፤መምህራንና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ ግንኙነት መፍጠር የተቻለበት አሰራር መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ጌትነት ገብረሚካኤል ገልጸው አገልግሎቱም በትምህርት ቤት ደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ በአዲስ አበባም ሆነ በሀገር በአቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡
ርዕሰ መምህሩ አክለውም ትምህርት ቤቱ 8,500 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ቀደም ሲል ከተማሪ ወላጆች ጋር የነበረው ግንኙነት በደብዳቤ ስለነበር ለወረቀትና ቀለም ሲወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ማስቀርት ከማስቻሉ ባሻገር የሰው ጉልበትና የማባዣ ማሽን አቅምን በአግባቡ ለመጠቀም መቻሉን ገልጸው ለአገልግሎቱም በወር 2,800 ብር ለኢትዮ ቴሌኮም እንደሚከፈል አስረድተዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጀመሩ መምህራን በአይ ሲቲ ላብራቶሪ የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት ከመቻላቸው ባሻገር ትምህርት ቤቱ በውጭ ሀገር ከሚገኙ መሰል ትምህርት ቤቶች ጋር የስራ ግንኙነት ፈጥሮ ልምድ መቅሰም መቻሉን አቶ ጌትነት አስታውቀዋል፡፡
መምህር ዳንኤል መኮንን በትምህርት ቤቱ የሒሳብ ትምህርት መምህር ሲሆኑ ትምህርት ቤቱ አጭር የጽሁፍ ማስተላለፊያ መስመሩን መጠቀም መጀመሩ ከመምህራንም ሆነ ከሌሎች የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ባሉበት በቀላሉ መገናኘት እንዳስቻለው ሲገልጹ ተማሪ ዮርዳኖስ ገብረኪዳን በበኩላ ቀደም ሲል ከትምህርት ቤት ለወላጆቻቸው የሚላኩ መልዕክቶች በወረቀት እንደነበሩ ገልጻ አሁን ግን በአጭር የጽሁፍ መላኪያ ቁጥሩ በቀላሉ መገናቸት መቻሉን ጠቁማለች ፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
