ቀን 8/6/2015 ዓ.ም

የሸገር ባስ አውቶብሶች ለመምህራንና ትምህርት አመራሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ተወሰነ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ሙያ ላይ የሚገኙ መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን ከዚህ ቀደም የከተማ አስተዳደሩ የአንበሳ አውቶብስ ብቻ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም በቅርቡ የአንበሳ ባስና የሸገር ባስ ውህደት በመፍጠራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው አለሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አመራሮች ባደረጉት ውይይት በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ሙያ ላይ የሚገኙ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ከሰኞ ማለትም ከ13/6/2015 ዓ.ም ጀምሮ የሸገር ባስን አሁን እየተጠቀሙበት ባለው መታወቂያ መጠቀም እንዲችሉ ተወስናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሎሎች ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ ከመምህራን የቀረቡ ጥያቄዎችን በተመለከተ በመድረኩ ላይ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይ ችግሮችን በጥናት ለመፍታት እንዲቻል አጥኚ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s