“በኢትዮጵያ አዲስ ከተቀረጸው ስርዓተ ትምህርት ታንዛኒያ ጠቃሚ ግብዓት አግኝታለች “የታንዛኒያ የትምህርት ፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ቋሚ ምክትል ሚኒስትር
የታንዛኒያ የትምህርት ፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን በትምህርት ሚኒስቴር የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርጓል ።
12 አባላት ያሉት የታንዛኒያ የልዑካን ቡድን በቅድመ መደበኛ ፣ በሁለተኛ ደረጃ ፣ በቴክኒክና ሙያና በዩኒቨርስቲዎች በመዘዋወር ምልከታ አድርጓል።
ልዑካን ቡድኑን የመሩት የታንዛኒያ ሪፐብሊክ ቋሚ ምክትል የትምህርት፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ጀምስ ኤፒፈን ጋብርኤል ሞድ በጉብኝቱ ወቅት በኢትዮጵያ አዲስ ከተቀረጸው ስርዓተ- ትምህርት አገራቸው በርካታ ጠቃሚ ልምዶችን እንዳገኘች ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት አገራቸው ታንዛኒያ የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያና ክለሳ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለአገር በቀል ዕውቀቶች ፣ ለተግባርና ሙያ (ክህሎት) ትኩረት የሰጠ መሆኑንን ተናግረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) በበኩላቸው ነባሩ ስርዓተ ትምህርት መለወጥ ያስፈለገው በንድፈ ሀሳብ የታጨቀና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑ ነው ማለታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ዘግባል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/