ለክርስትና ዕምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሀይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በየዓመቱ በደማቅ ስነ-ስርዓት የሚከበር ክብረ በዓል ከመሆኑም ባሻገር ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር ማህበራዊ እሴት ነው፡፡ይህ ደግሞ ፍቅርን በማብዛት፣ ወንድማማችነትን በማሳደግ እና እርስ በእርስ መተዛዘንን በማጠናከር ለሀገር ግንባታ ትልቅ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች በአለም ቅርስነት የተመዘገበ በአለም አደባባይ የምንታወቅበት ድንቅ ባህላችን ነው። በዓሉ የሀገራችን ብቻ ሳይሆን አለም በድምቀት የሚያከብረው የጋራ ኩራታችን የሆነ ታላቅ በዓላችን በመሆኑ ክብረ በዓሉ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በሠላም እንዲጠናቀቅ ሁላችንም ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ጥር 10 እና 11 ቀን የሚከበሩት የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር የሀገርን መልካም ገጽታን ከመገንባት እና የቱሪስት ፍሰትን ከማጎልበት አንጻር ጉልህ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ በማስተናገድ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ በተለይም ደግሞ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፀጥታ አካላት ጋር እጅና ጋንት በመሆኑ መስራት ይኖርባችዋል።
በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለአየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን እመኛለሁ፡፡
አመሰግናለሁ!
ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/