በተደረጉ የድጋፍ፣ ክትትልና ሱፐርቪዥን ስራዎች ግኝቶች ላይ ውይይት ተካሄደ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በግል ት/ቤቶች ባደረገው ድጋፍ፣ ክትትልና ሱፐርቪዥን ላይ ያገኘውን ግኝት የጋራ ያደረገ ሲሆን በመድረኩ የቅድመ መደበኛ፣ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ የግል ት/ቤት ባለሀብቶች፣ ርዕሰ መምህራን፣ ወላጅ ተማሪ ማህበር (ወ.ተ.መ) የክ/ከተማና ወረዳ የት/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ እንዳሉት በየጊዜው የሚከፈቱ የግል ት/ቤቶች መኖራቸው ወላጅ ልጆቹን በፈለገው ት/ቤት እንዲያስተምር ይረዳዋል ብለው በየጊዜው በሚደረጉ ድጋፍ፣ ክትትልና ሱፐርቪዥን ላይ የታዩ ክፍተቶችን በማረም ጠንካራ ጎኖችን በተሻለ መልኩ በማስቀጠል ወላጅ በኃላፊነት የሰጣቹን ተማሪ ለነገ ሀገር ተረካቢና በዕውቀቱ ሚተማመን ዜጋ ማድረግና መፍጠር ይገባል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም የግል ትምህርት ቤቶች ስብዕና በማስጠበቅ የመማር ማስተማር ሂደቱንም የተስተካከለ ማድረግ፣ ለተቋሞችም የሚያስፈልጉ ግብአቶችንና የሰው ኃይል በማሟላት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይኖርባቹዋል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በግል ት/ት ተቋማት ላይ ድጋፍ፣ ክትትልና ሱፐርቪዥን መደረጉ እያንዳንዱን ችግሮቻችን ለይቶ ማየትና ማስተካከል ያስችላል በመሆኑም የት/ቤቶችን አሰራር እንዲቀየር፣ አግባብነት ያለው የተማሪዎች ቅበላ እንዲኖርና ጥራቱንና ስርዓቱን የጠበቀ የመማር ማስተማር ሂደት የተስተካከለ እንዲሆን ለማስቻል የሚመለከተው አካል በማሳተፍ የተማሪዎችን ህልውና ማስጠበቅ የወላጆችንም ልፋት ዋጋ እንዲያገኝ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
ተሳታፊዎቹም የተደረገላቸው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም ሱፐርቪዥን መደረጉ ለቀጣይ አሰራር እንደሚረዳቸው መጥቀሳቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ዘግባል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/