ቀን 21/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሚገኘው ኤፍ ኤም 94.7 የሬዲዮ ጣቢያ ጉብኝት አካሄደ።

በጉብኝቱ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሚኒ ሚዲያ ክበብ ተጠሪዎችና አባላትን ጨምሮ የሬዲዮ ትምህርት ተጠሪዎች እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮችና የክፍለ ከተማ የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ጉብኝቱ በዋናነት የሚኒሚዲያ ክበባቱ አባል ተማሪዎቹም ሆኑ ተጠሪ መምህራኑ በሬዲዮ ጣቢያው ያለውን አሰራርም ሆነ የስቱዲዮ አደረጃጀት በመመልከት በየትምህርት ቤቶቻቸው በተሻለ ሁኔታ ክበባቱን እንዲያደራጁ ታስቦ መካሄዱን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ቤኩማ ደበሎ ገልጸው የሚኒ ሚዲያ አባል የሆኑት ተማሪዎች መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ዕውቀት እንዲኖራቸው ጉብኝቱ አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም በሬዲዮ ጣቢያው   የተመለከቱት የስቱዲዮ አደረጃጀትም ሆነ አሰራር በየትምህርት ቤቶቻቸው ከበባቱ በተሻለ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ ከማስቻሉ ባሻገር ወደፊት በጋዜጠኝነትና ተያያዥ ሙያዎች መስራት ለሚፈልጉ ተማሪዎች ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s