ሌብነትን/ሙስናን/ ሀገራዊ የህልውና አደጋ አድርገን ልንታገለው ይገባል፡- የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከትምህርት ማህበረሰቡ አባላት ጋር “ሌብነትን መታገል በተግባር” መሪ ሃሳብ ሙስናን መታገል በሚቻልበት ጉዳይ ከመምህራን፣ ከተማሪዎችና ከወተመህ አባላት ጋር የተሳካ የንቅናቄ መድረክ መካሄዱን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ አስታውቀዋል፡፡
በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ ሌብነት/ሙስና/ ሃገር እድገትን የሚያቀጭጭ የእድገት ፀር በመሆኑ ሁላችንም በተባበረ ክንድ ልንታገለው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱልሰመድ ሻሚል በበኩላቸው ሌብነትን/ሙስናን/ ሃገራዊ የህልውና አደጋ አድርገን ልንታገለው የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ የት/ት ዘርፉ ባለሙያዎችም የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው መግለጻቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው ወረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/