እንኳን ደስ አላችሁ! አለን!
በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ለ7ኛ ጊዜ በተካሄደው የሳይንስ ዓውደ ርዕይ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሁሉም ክልሎች ጋር በተማሪዎች እና በመምህራን የፈጠራ ስራዎች በመወዳደር 2ኛ ደረጃን በመያዝ በማጠናቀቁ ሽልማት ተበረከተለት፡፡
የዓለም ሳይንስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሂሳብ ፣ በሳይንስና ስነ-ጥበብ ማበልጸጊያ ዴስክ ከዩኒስኮ ፣ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ፣ ከስቴም ሲነርጂ እና ከስቴምፓወር ጋር በመተባበር ከጥቅምት 27 እሰከ ህዳር 2/2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስ ዓውደ ርዕይ ላይ በቀረቡ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች እና መምህራን የፈጠራ ስራዎች በተደረገው ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 2ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል፡፡
ይህንንም በማስመልከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንኳን ደስ አላቸሁ! አለን! ያሉ ሲሆን ሀላፊው አክለውም ለዚህ ውጤት መመዝገብ የሚናቸውን ለተመጡ አካላት በሙሉ ምስጋና በማቅረብ መሰል ውጤቶች ለቀጣይ ስራዎች ብርታትና ጉልበት በመሆን ለሀገር ፣ ለአፍሪካ ብሎም ለአለም በቀጣይ የተሻለ የሳይንስና የፈጠራ ስራ ለመስራት እና አስተዋጽዎ ለማበርከት መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠጥ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/