አለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር ተካሄደ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች በመተባበር ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር አካሂደዋል።
ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና የክልል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸው ለዳኞች ገለጻ በማድረግ አስገምግመዋል።
የውድድሩ ውጤትም በአውደ ርእዩ መዝጊያ ወቅት እንደሚገለጽና ከየምድቡ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።
አውደ ርእዩም በነገው እለት ለህዝብ ክፍት በመሆኑ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ግቢ በመገኘት መጎብኘት እንደሚቻል ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/