አዲስ አበባ ‘በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም’ ከ133 ሀገራት ከቀረቡ 251 ተምክሮዎች ውስጥ በመወዳደር 1ኛ በመውጣት አሸንፋለች።
እንኳን ደስ አለን!
አዲስ አበባ ‘በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም’ ምርጥ ተሞክሮ የ8ኛው የMUFPP (Milan Urban Food Policy Pact) ግሎባል ፎረም ዘላቂ አመጋገብ እና ስነ-ምግብ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆነች።
አዲስ አበባ ይህንን ሽልማት ያገኘችው ጥቅምት 17/2022 (እ.ኤ.አ) በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ ” “Food to Feed the Climate Justice: urban food solutions for a fairer world “በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የ8ኛው የMUFPP ግሎባል ፎረም መድረክ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ133 ሀገራት ከቀረቡ 251 ተምክሮዎች ውስጥ በመወዳደር እና 1ኛ በመውጣት አሸንፋለች።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሰው የሚሰጥ ፖሊሲ በማውጣት እየተከናወነ ስላለው ሰው ተኮር ተግባራት ከMUFPP ፈራሚ ከተሞች ለመጡ ከንቲባዎች እና ተሳታፊዎች ልምድ አካፍለዋል።
የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ለወላጆች እፍይታን ከመስጠት ባለፈ ተማሪዎች ለትምህርታቸው ትኩረት እንዲሰጡ ፣ መጠነ መድገም እና ማቋረጥ እንዲቀንስ በጥቅሉ የትምህርት ውጤታማት እንዲጎለብት ከማስቻሉም ባለፍ ለተማሪ ወላጆች እና ለከተማ ማህበረሰቡ ሰፊ የስራ እድል የፈጠረ ነው፡፡
ይህ ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላበረከቱ በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና ባለሙያዎች ፣ ለከተማ አስተዳደሩ ፣ ለመምህራን ፣ ለተማሪዎች ፣ ለመጋቢ እናቶች እና ለትምህርት ባለድርሻ አካላት በሙሉ ለተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/