የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎችን በቅርቡ ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀውን የሳይንስ ሙዚየም አስጎበኘ።
በጉብኝቱ ከተማሪዎች ባሻገር መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ መሆናቸውን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሳምራዊት ቅባቱ ገልጸው በጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑ ተማሪዎች በሙዚየሙ የሚገ ኙ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ተመልክተው በቀጣይ በትምህርታቸው ታግዘው ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎችን መስራት እንዲችሉ እንደሚያግዛቸው አስረድተዋል።
ኃላፊዋ አክለውም የሳይንስ ሙዚየሙ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ የሚያሳዩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች የሚገኙበት እንደመሆኑ በቀጣይም በሙዚየሙ ተመሳሳይ ጉብኝት በቀሪ ተማሪዎችና መምህራን እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
የሳይንስ ሙዚየሙን ለመጎብኘት እድሉን ያገኙ ተማሪዎችና መምህራን በበኩላቸው በሙዚየሙ የተመለከቷቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከፍተ ኛ አግራሞትን እና ተነሳሽነትን እንደፈጠሩባቸው ጠቁመው በሙዚየሙ ጉብኝት እንዲያደርጉ እድሉን ላመቻቸላቸው የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ምስጋና አቅርበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/