ቀን 20 /1/2015 ዓ.ም

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት የምስጋና በዓል በመሆኑ በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን ለማጎልበት ያግዛል፡፡

ኢሬቻ በህዝብ መሰባሰብ አብሮነትን በሚያሳይ ደረጃ ደምቆ የሚከበር ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን የጨለማ ጊዜ አሳልፈኸን ብራን ልምላሜን ውበትን ያሳየኸን፤ ተፈጥሮን ሕይወትን መልሰህ  ያጎናፀፍከን፤ መሬቱን በልምላሜ፣ ድፍርሱን በጥራት የተካህልን፤ ወደ ብርሃንና መልካም ዘመን ያሻገርከን ፈጣሪያችን ምስጋና ይገባሃል በማለት ምስጋናውን የሚያቀርብበት እና ላጠፋነው ነገር ሁሉ ይቅር በለን እያለ ከፈጣሪው ጋር ጥልቅ ተፈጥሯዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት ታላቅ በዓል ነው።

ኢሬቻ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር የአንድነትን ፣ የብሮነትን እና የመተባበርን ስሜት የሚፈጥር ታላቅ በዓል በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ይህንን በሚያሳይ ደረጃ ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢሬቻ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሀብት በመሆኑ ሁሉም በእኔነት ስሜት በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የጋራ እና ከፍተኛ በሆነ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪዩን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

                   አመሰግናለሁ!

                 ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

                 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s