ቀን 7/1/2015 ዓ.ም

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በተዘጋጀው የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍና የመምህር መምሪያ ለተሳተፉ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ።

በእውቅና እና የምስጋና መርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና የ1ኛ ደረጃና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የከተማውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበና ነባሩ ስርዓተ ትምህርት ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ባሻሻለ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ስርዓተ ትምህርቱ የመንግስት ዋነኛ ትኩረት የሆነውን ሁለንተናዊ ዕውቀት ያለውና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት በመጥቀስ በመጽሀፍ ዝግጅቱ ለተሳተፉ መምህራን ፣የትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው በዋናነትም ለአንደኛ ደረጃና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት የሚያገለግሉ የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ማዘጋጀት መሆኑን በመግለጽ መጽሀፍቱ በራሳችን መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች የተዘጋጁ በመሆናቸው ከፍተኛ ወጪ ከመቀነሳቸው ባሻገር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ማስቻሉን አስታውቀዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም ስርዓተ ትምህርቱ በ2014 ዓ.ም በ44 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ተደርጎ ዘንድሮ በሁሉም 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ የመጽሀፍ ዝግጅቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ በጀት ከመመደብ ጀምሮ ላደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና ከማቅረባቸው ባሻገር በመጽሀፍ ዝግጅቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለተሳተፉ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

+47

6,775

People reached

894

Engagements

Boost post

132132

11 Comments

16 Shares

Like

Comment

Share

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s