ቀን 4/13/2014 ዓ.ም

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በአገልጋይነት ቀን ለተማሪዎች እና ለተማሪ ወላጆች የአዲስ ዓመት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ “አገልጋይነት ጀግንነት ነው” በሚል መሪ ቃል ከ150 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከ300,000 ብር በላይ በሚገመት ገንዘብ እንደ ዘይት ስኳር ፣ ዶሮ ፣ ዱቄት እና የመሳሰሉ የአዲስ አመት የበዓል ስጦታዎችን ማበርከቱን የጽ/ቤቱ ሀላፊዋ ወ/ሮ ባዩማ ወርቁ ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ ባዩማ ጽ/ቤታቸው ይህን የበጎነት ተግባር ለማስቀጠል  ህብረተሰቡን ፣ በጎ አድራጊ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በበዓላት እና ከበዓላት ውጪ ባሉ ጊዚያትም  አበክሮ እንደሚሰራ በመግለጽ ይህንን የበጎነት ተግባር በማስተባበር ከፍተኛ አስታዋጽኦ ላበረከቱ የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት አካላት እና የወተመህ አባላት  ያላቸውን ልባዊ ምስጋናና እና አድናቆትም ገልጸዋል፡፡

በዝግጅቱ  ላይ ተገኝተው ንግግር  ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊዋ ወ/ሮ ሰብለም በተመሳሳይ ዝግጅቱን ላስተባበሩ አካላት ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ 2014 ዓ.ም እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንደመር ውጤት ማምጣት እንደምንችል እና ጠላቶቻችን መና ማድረግ እና ታሪክ መስራት እንደምንችል ያሳየንበት ዓመት ነው ብለዋል፡፡

አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል!

አገልጋይነት ለሀገር ክብር 

አገልጋይነት ክብርም፤ታላቅ ስብእናም ነው!

ዝቅ ብለን አገልግለን ፤ታላቅ ሃገር እንገነባለን!

ሀገርን ማገልገል ታላቅ ክብር ነው!!

ሀገሬን መቼም፣ የትም በምንም ሁኔታ አገለግላለሁ! 

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s