ቀን 3/13/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ያዘጋጀውን የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ይዘት ከየክፍለ ከተሞቹ ለተውጣጡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

የመጽሀፍ ማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ በሁለት ዙር ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአማርኛና አፋን ኦሮሞ የትምህርት ዘርፍ ለሚያስተምሩ መምህራን በሁሉም የትምህርት አይነቶች በተዘጋጁ የመማሪያ መጽሀፍ ይዘቶች ዙሪያ  ሲሆን ይዘቱን ቀደም ብሎ በመጽሀፍ ዝግጅቱ የተሳተፉ መምህራን በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኙና በቀጣይ መምህራኑ ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ በየክላስተሩ ለሌሎች መምህራን በተመሳሳይ የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩ ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ተችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የመጽሀፍ ማስተዋወቅ መርሀ ግብሩን ዳግማዊ ሚኒሊክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን የመጽሀፍ ትውውቁ በዋናነት መምህራኑ የመጽሀፉን ይዘትና ፍሰት ገምግመው በቀጣይ ስርዓተ ትምህርቱን ማበልጸግ የሚያስችሉ ሀሳቦችን ማቅረብ እንዲችሉ የሚረዳ ከመሆኑ ባሻገር መምህራኑ በየክላስተሩ ለባልደረቦቻቸው ተመሳሳይ ግንዛቤ መፍጠር እንዲችሉ የሚረዳቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎቹ አቶ አድማሱ ደቻሳና አቶ ሳምሶን መለሰ እንዲሁም የቢሮው ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ታትመው ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ የሆኑ የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፎችን ምልከታ አድርገዋል።

ሰላም ለኢትዮጵያውያን!

የኢትዮጵያ የሰላም አቋም ዘላቂና የማይናወጥ ነው!

የሰላማችን ዘብ ጀግናው ሰራዊታችን!

ሰላም ለሁለንተናዊ እድገታችን

እኔ የሰላም ዘብ ነኝ! 

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s