ጳጉሜን 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን
በጎ ፍቃደኝነት ከበጎ ህሊና የሚመነጭ የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ ከራስ አልፎ ለሌሎች የመሆንን አሳቢነትን ፣ አካፋይነትን አቋዳሽነትን ፣ ተባባሪነትን ፣ እኔ ብቻ አለማለትን እና ተጋግዞና ተደጋግፎ መኖርን የሚገልፅ ከፍ ያለ ስብዕና መገለጫ ነው፡፡
በጎ ፈቃደኝነት የህብረተሰብን አኗኗርን ሊያሻሽሉና ሊለውጡ እንዲሁም ሃገርን ሊያሳድጉ የሚችሉ ተግባራትን በራስ ተነሳሽነት ተጨማሪ ክፍያ ወይም ምንዳ ሳይጠየቅበት የሚከወን ተግባር ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ይህ የእርስ በርስ መደጋገፍ ለዘመናት አብሮን የኖረ ባህላችንም ጭምር ነው፡፡
ሁላችንም በበጎ ፈቃድ ካለን እውቀትና ሃብት ለማህበረሰባዊ ለለውጥ በማዋል የየራሳችንን አሻራ በማሳረፍ የከተማችን ብሎም የሃገራችንን እድገት ማፋጠን እንችላልን፡፡ ለተደጋገፉና ለተባበሩ እጆች ለውጥ ቀላል ነው፡፡በጎ ፈቃደኝነት ለራስ እርካታ ለሀገር እድገት ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡
የሀገሬን ህልውና ለማስከበር በበጎ ፈቃደኝነት ሁለንተናዊ ድጋፍ አደርጋለሁ!
መልካም የበጎ ፍቃድ ይሁንልን!
በጎነት መልሶ ይከፍላል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን አብዝቶ ይባርክ!
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
