ቀን 28 /11/2014 ዓ.ም

ዕድለኛዋ የጸሃይ ጮራ አንድኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት

ላለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ አስተምረዋል። ረጅሙን ጊዜያቸውን ያሳለፉት ግን በጸሃይ ጮራ አንድኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በመምህርነት ነው። የ7 እና 8ኛ ክፍል ባዮሎጂ መምህር ናቸው። መምህርት አስናቀች አበበ።

“መምህርነት ለእኔ የተፈጠረ ሙያ ነው። ከዚህ ሙያ ውጪ ስራ ያለም አይመስለኝም” ይላሉ ለመምህርነት ያላቸውን ፍቅር ሲገልጹ።

 “ትውልድን መቅረጽ፣ መሰረቱን መገንባት የመምህር ሙያ ነው። እዚያ ላይ የተበላሸ የዜጎች ግንባታ ወደላይ መውጣት ያዳግተዋል” ይላሉ።

“በማስተምርበትና በምኖርበት ሽሮ ሜዳ አካባቢ ያሉ ትምህርት ቤቶች ኢትይጵያን መመልከቻ መስኮቶች ናቸው…” ይላሉ የመምህርነት ትሩፋታቸውን ሲናገሩ።

 “ከጥቂት አመታት በፊት ለመማር እየመጡ የሚበሉት ሳይኖራቸው የሚቸገሩ በርካታ ተማሪዎቻችንን በመደገፍ ነበር ደመወዛችንን የምንጨርሰው። ባዶ እጄን ቤቴ የገባሁበት ጊዜ ነበር። ችግርኛ ተማሪዎች በጓደኞቻቸው ዘንድ ዝቅ ብሎ ላለመታየት ባዶ የምሳ እቃ ይዘው መጥተው በምሳ ሰዓት ሌላ ቦታ ይቆዩና ከበሉት ጓደኞቻቸው ጋር እቃቸውን አጥበው ልክ ወደክፍል ሲገቡ ማየት በጣም ያሳቅቅ ነበር። እንዳይርባቸው ብለው ጸበል ጠጥተው የሚውሉ በርካታ ችግረኛ ተማሪዎች ነበሩ። ይህንን ችግር በመካፈል ከማስተማሩ ጎን ለጎን እነሱን የመርዳት እና የመመገብ ሰብዓዊ ሃላፊነት እኛ ላይ ነበር የወደቀው። ዛሬ ሁሉም ነገር በመስተካከሉ ደስ ብሎኛል፣ መምህርነት ለኔ ትርግሙ ይኼ ነው” ይላሉ መምህርቷ ….ሙያው ሰብዓዊነትም ጭምር መሆኑን ሲገልጹ።

መምህርት አስናቀች አበበ የቡና ባንክ ደንበኛ ከሆኑ ገና ስድስት ወራቸው ነው። “አንድ ቀን የባንኩ ሰራተኞች ወደትምህርት ቤት መጥተው “የሽልማት ማበረታቻ ያለው የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ቁጠባ መርሃግብር ተጀምሯልና ተሳተፊ” አሉኝ…..ቡና ባንክ መምህራንን አስቦ ፣ ለሙያው ክብር ሰጥቶ በስማችን የቁጠባ መርሃ ግብር በመጀመሩ ብቻ ከፍ ያለ ደስታ ስለተሰማኝ ወዲያውኑ ነበር ሂሳብ የከፈትኩት። ከዚያ በኋላም መቆጠብ ጀመርኩ።” ብለዋል።

እነሆ ሁለተኛው ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅና ዕጣ ሲወጣ ዕድል ወደርሳቸው ቀረበችና የ1ኛው ዕጣ የ2021 ሱዙኪ ዲዛየር መኪና አሸናፊ ሆኑ። ሽልማታቸውንም ዛሬ በግዮን ሆቴል በተካሄደው ደማቅ ስነስርዓት ከባንኩ መቀበላቸዉን ከቡና ባንክ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s