የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቶ በመልዕክታቸዉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሰኔ 27-29/2014 ዓ.ም ድረስ በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71,832 ተማሪዎች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ፈተናዉን ጀምረዉ እስካጠናቅቁ ድረስ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲሁም ተማሪዎች በስነ ልቦና ዝግጁ ሆነው ፈተናቸውን እንዲወስዱ ያላሰለሰ ጥረት ስታደርጉ ለቆያችሁ እና ዛሬ ያለምንም እንከን ፈተናዉ ፍጻሜ ላይ እንዲደርስ ላደረጋችሁ በከተማ እና በየደረጃዉ ፈተናዉን ለማስፈጸም ለተደራጃችሁ የኮማንድ ፖስት አባላት ፣ ለትምህርት አመራሮች እና ባለሙያዎች ፣ ለመምህራን ፣ ለወላጆች ፣ ለተማሪዎች ፣ ለፈታኞች ፣ ለሱፕርቫይዘሮች ፣ ለጣቢያ ሀላፊዎች እና ለሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ልባዊ ምሰጋናዩን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ሀላፊ እንደገለጹት ፈተናዉ ከህትመት እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ያለምንም እንከን እንዲደርስ ብሎም ያለምንም ችግር ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሌት ተቀን ሀያ አራት ሰሃት ላገለገሉ የጸጥታ አካላት እና ፖሊሶች ሁልጊዜም ከትምህርት ቢሮ ጎን በመቆም ትውልድን በመቅረጽ ስራ ውስጥ ላሳረፉት አበርክቶ ማሳያ እና ታላቅ ተግባር ነዉ በማለት ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን የከተማችን ተማሪዎች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ደረጃ እየወሰዱ መሆናቸዉን እና የከተማዉ ማህበረሰብም ይህን አውቆ ተገቢዉን እገዳ እንዳደርግ የማህበረሰብ ንቃት እንዲፈጠር ላደረጋችሁ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎችም ምስጋና ያቀረቡት የቢሮ ሀላፊዉ የአመቱ የትምህርት ማጠናቀቂ እና የትምህርት ማህበረሰቡ ታላቅ የአረንጋዴ አሻራ ቀን /Green legacy day/ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም “አሻራችን ለትውልዳችን!” በሚል መሪ ቃል በየካ ሚሊኒየም ፓርክ ከጠዋቱ 12 ሰሃት ጀምሮ የሚከናወን በመሆኑ ፈተናዉን የወሰዱ ተማሪዎች እና በየደረጃዉ የሚገኙ የትምህርት መዋቅር አካላት በቦታዉ እንዲገኙ እና አሻራችሁን እንዳሳርፉ ጥራቸዉን በማቅረብ ለተማሪዎች መልካም ውጤትን ተመኝተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!







