ቀን 27/10/2014 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የመጀመሪያው ቀን ፈተና ያለምንም እንከን መካሄዱ ተገለጸ።

የክፍለከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ አበራ እና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሳምራዊት ቅባቱን ጨምሮ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እሸት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፈተናው በ16 የፈተና ጣቢያዎች 6532 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሪት ሳመራዊት ቅባቱ ገልጸው ፈተናውም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲሰጥ መዋሉን በመጥቀስ ለዚህም የጸጥታ አካላትን ጨምሮ የሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተዋጾ ላቅ ያለ መሆኑን አታውቀዋል ።

የእሸት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፈተና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ገብረጻድቅ ቢያዝን በበኩላቸው በጣቢያው ከአራት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 447 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቅሰው ፈተናውም ከማለዳ ጀምሮ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ያለምንም እንከን ሲካሄድ ቆይቶ መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a comment