የከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለት አራተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር በይፋ አስጀምሯል::
በአዲስ አበባ ከተማ አራተኛውን ዙር አረንጓዴ አሻራን በይፋ የማስጀመር መረሀ ግብር ላይ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ ኡመር ሁሴን፣የኢፌዴሪ ሴቶች ሕጻናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኤርጓጌ ተስፋዬ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙሉቱ እና ሌሎች ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሲቪክና ማህበራት ተወካዮች ፤ የሃይማኖት መሪዎች ፣ አርበኞች አርቲስቶች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
አረንጎዴ አሻራ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አነሳሽነት የዛሬ አራት ዓመት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በከተማችን በሚፈለገው ደረጃ ዘርፈ ብዙ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል ።
ተፈጥሯዊም ሆነ የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድበን ሀገራችንንም ሆነ ከተማችንን አረንጓዴ በማልበስ ለትውልድ የሚሻገር አሻራ በአንድነት እያኖርን እንቀጥላለን ያሉት ከንቲባ አዳነች በሁሉም ረገድ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በቅንጅት መሥራት ይኖርብናል ብለዋል ። አክለዉም እኛ ልክ አንድ አንድ ልብ መካሪና ቃል ተናጋሪ ሆነን ችግሮቻችንን ከምንጫቸው በብልሀት እያደረቅን መትከላችንንና ልማታችንን አጠናክረን በማስቀጠል ለትውልድ በሁሉም ረገድ የተሻለች አገር እንገነባለን ሲሉ ተናግረዋል ።
መብላት እስካላቆምን ድረስ መትከልና መሥራት አናቆምም ያሉት ከንቲባ አዳነች አጠቃላይ የልማት ሥራዎቻችንን የምናከናውነው መጪውን ትውልድ ታሳቢ እያደረግን ብለዋል ።
በመጨረሻም ከንቲባ አዳነች ከሚያወራ የሚሰራ ፤ከሚያማ የሚያለማ ፤ከሚገፋ የሚያቅፍ ፤ከሚጠላ የሚወድ ከሚገድል የሚያድን ትውልድን የመገንባት አንዱ አካል ነው በማለት ገልፀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!










