ቀን 11/10/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት ከሰኔ 9 እስከ 11/2014 ዓ.ም የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዟችንን በሳይንስ የፈጠራ ስራ እውን እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል በድምቀት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት በፎቶ።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አቀፉ የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ ከመክፈቻው ጀምሮ እስከ መዝጊያ ድረስ በደማቅና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው የዘንድሮው አውደ ርዕይ ሌሎች መሰል መርሀ ግብሮችንም በድምቀት ማክበር እንደምንችል ያሳየ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ላለፉት ሶስት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ  ዘርፍ ባለምጡቅ አእምሮ ትውልድ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ያሳየ  መርሀ ግብር ከመሆኑ ባሻገር የሀገራችንን አንድነት የሚያጎለብቱ ትዕይንቶች የታዩበት መሆኑንም አስረድተዋል።

የመዝጊያ መርሀግብሩ የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ባስተላለፉት መልዕክት በአውደ ርዕዩ  በተማሪዎችና መምህራን ተዘጋጅተው ለዕይታ የቀረቡት የሳይንስ ፈጠራ ስራዎች ሀገራችንን ወዳሰበችው የብልጽግና ጉዞ የማሸጋገር አቅም እንዳላቸው ገልጸው ቢሯቸው ከትምህርት ሴክተሩ ጋር በጋራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ በአውደ ርዕዩ በየትምህርት ደረጃው ውድድር በተደረገባቸው የፈጠራ ስራዎችና በሽብርቅ  አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ክፍለከተሞች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ለመርሀ ግብሩ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s