የአራብሳ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በተለያየ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
በለሚ ኩራ ክፍ ከተማ አስተዳደር ስር ባለው ወረዳ 04 አራብሳ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት ለሦስት ወራት በዘመናዊ ዳንስ ፣ በባህላዊ ጭፈራ ፣ በሙዚቃ መሣሪያ አጨዋወት እና በምልክት ቋንቋ ስልጠና የወሰዱ ተማሪዎችን አስመርቋል።
ተመራቂ ተማሪዎችም በሠለጠኑበት ዘርፍ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ትዕይት ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ደግሞ በምልክት ቋንቋ ዘርፍ የተመረቁ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን ፣ ስለ አባይ የተዜሙ ሙዚቃዎችን እና የግጥም ስንኝ ንባብ በምልክት ቋንቋ አቅርበዋል።
በዚህ የምረቃ ስነ-ስርት ላይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወሰን ፀጋዬ እና የወረዳው አመራሮች እንዲሁም የተመራቂ ተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።
የምረቃ ስነ-ስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ጌትነት ገ/ሚካኤል በእንግግራቸው ሲናገሩ በመጀመሪያ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችን ማለትም ከስምት ሺህ ዘጠኝ መቶ(8,900) ተማሪዎች እና ሶስት መቶ ሠላሳ አምስት(335) መምህራንን እንዲሁም ከዘጠና ዘጠኝ(99) በላይ የሆኑ ደጋፊ ሠራተኞችንም ትምህርት ቤቱ እንደያዘ በተጨማሪ ገልፀው ትምህርት ቤቱን በጉልበት ፣ በእውቀት እንዲሁም በገንዘብ ለደገፉ የአካቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩ መምህራንን እና ሰልጣኝ ተማሪዎች የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰቶ የምረቃው ስነ-ስርዓት ፍፃሜውን አገኝቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!






