“ፅዱ እና ውብ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች!” በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡
የጽዳት ዘመቻዉ የተከናወነዉ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ስር በሚገኘው የኢትዮ ቻይና ት/ቤት ላይ ነዉ፡፡
የእለቱ የፅዳት ዘመቻ ሰባተኛ ዙር ሰባተኛ ሳምንት መሆኑ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ፅዳትን ባህል እንዲያደርጉ ትኩረት ሰጥተዉ ሊሰሩ ይገባልም ተብላል።
በዚህ ፅዳት ዘመቻ ላይም ተማሪዎች እና የትምህርት ቤቱ መምህራን በዋናነት ተሳታፊዎች ሲሆኑ በክብር እንግድነትም የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ምክትል ሀላፊ አቶ አበራ አፍራሳ ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙክታር ኢብራሂም እና የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እዮብ እሸቱ ተገኝተዋል።
በእለቱን በተማሪዎች የተዘጋጁ የፈጠራ ስራዎችም ቀርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




