የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የረመዳን ጾምን ሞክንያት በማድረግ የአፍጥር መርሀ-ግብር አከናወነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት ባከናወነው የአፍጥር መርሀ-ግብር የቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የቢሮ ሀላፊ አማካሪዎች ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ እና በመዋቅሩ የሚገኙ የትምህርት ባለሙያዎች እና ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በአፍጥር መርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው የረመዳን ጾምን ሞክንያት በማድረግ የሚያከናውነው የአፍጥር መርሀ-ግብር የቢሮው ባህል ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሞክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር በበኩላቸዉ የመረዳዳት እና የመስጠት ባህላችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




