በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 5 ትምህርት ጽ/ቤት ስር በሚገኙት በህብር ፣ በሊዛ ፣ በዶንቦስኮ እንዲሁም በጎፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች “ትምህርት ቤቴን አጸዳለሁ ጽዱ እና ውብ በሆነ ት/ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻ ተካሄዳል፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም ባስተላለፋት መልዕክት የዛሬ ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች በመሆናቸው ባማረ እና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እንዲማሩ ሁሉም ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶችን መደገፍ እንደሚገባዉ ገልፀዋል።
አቶ ተወዳጅ አክለውም ተማሪዎች የማጽዳት ልምድ እንዲያዳብሩ በየሳምንቱ በት/ቤቶች የጽዳት ዘመቻ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን ትምህርት ቤቶችን የጽዳቱ አንድ አካል አድርጎ መካሄዱ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም የሀብት ምንጭን ማድረግ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል።
በጽዳት ዘመቻዉ ላይ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት ኤጀንሲ አማካሪ አቶ መለሰ ደምሴን ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
