በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አሳይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አሳይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጠዋቱ መርሀ ግብር ተማሪዎችና የትምህርት ቤት ማህበረሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል ።
በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ፣ የትምህርት ቢሮ የፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ፣ የየካ ክፍለ ከተማ አመራሮች ፣ የትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ባደረጉት ንግግር ስፖርታዊ እንቅስቃሴን በየትምህርት ቤቶች የዘወትር ተግባር በማድረግ በተማሪዎች ላይ የዕርስ በርዕስ ግንኙነት እንዲጠናከር ከማድረግ ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን እንደ ሃገር በመፍጠር በኩልም ትምህርት ቤቶች የማይተካ ሚና ያላቸው በመሆኑ ቢሮው ዛሬም ለትምህርት ቤቶች ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና ተሳትፎዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁላችንም በጋራ የምንሰራው ቁልፍ ተግባራችን በመሆኑ በዚህ መልክ አስረኛው ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑን አቶ አብርሃም ገልፀዋል።
የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አስራ አንደኛውና የማጠቃለያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 11 / 2014 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ዳግማዊ ምንሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት የከተማዉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የስፖርት ቤተሰቦችና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
