የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጅ ማህበር (ተወማ ) የ2014 ዓ.ም የ6 ወር አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
በግምገማው የክፍለ ከተማ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የተመረጡ ክፍለ ከተሞችና የከተማው የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አብይ ተፈራ እንዳስታወቁት የተማሪ ወላጅ ማህበሩ በከተማ አስተዳደሩ በመማር ማስተማር ስራው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ ውይይት ማህበሩ በየክፍለከተማውም ሆነ በከተማ ደረጃ ባከናወናቸው ተግባራት ላይ በመወያየት በቀጣይ ጊዜያት የተሻለ ስራ ለመስራት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጅ ማህበር ሰብሳቢ ኢንጅነር ጌታቸው ሰጠኝ በበኩላቸው ማህበሩ ባለፉት 6 ወራት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱንና በዚህም በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን መፍትሄ እንዲያገኙ መስራቱን ገልጸው ማህበሩ ማከናወን የሚጠበቅበትን ተግባር በሚጠበቅበት ልክ ተግባራዊ ለማድረግ ያለበት የበጀት ውስንነት ችግር እንደፈጠረበትም አስገንዝበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
