ቀን 18/5/2014 ዓ.ም

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን አበይትና ቁልፍ ተግባራትን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገመገመ።

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ፣በተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም፣ እንዲሁም በመማር ማስተማሩ ሂደት ዙሪያ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት የክፍለ ከተማና የክላስተር ሱፐርቫይዘሮች፣ር/መምህራንና መምህራን፣የትምህርት ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት የውይይት መድረክ አካሄዷል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፋ አቶ አለልኝ ወንዴ ተቋሙ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያከናወናቸውን አበይትና ቁልፍ ተግባራት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ጽ/ቤቱ በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር፣ ተማሪዎች በእውቀትና በስነ-ምግባር ታንፀው የነገ ሃገር ተረካቢ ዜጋ  እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም በትምህርቱ ዘርፍ ተጠያቂነት ያለው አሰራር ከመዘርጋት ጋር በተያያዘ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘርፈ ብዙ ስራዎች  መከናወናቸውን በሪፖርቱ አመላክተዋል።

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ከተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም፣ የዩኒፎርምና የደብተር ድጋፍ በበጀት ዓመቱ መደረጉን የገለፁት ኃላፊው ተቋሙ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን  እንደ ሃገር የገጠመንን ፈተና በአሸናፊነት ለመወጣት የትምህርት ማህበረሰቡን በማስተባበር ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ከ7 ሚሊዮን ብር  በላይ  ሃብት በማሰባሰብ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ተማሪዎችንና መምህራንን በማስተባበር የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል የመሰብሰብ ስራ መሰራቱንም አቶ አለልኝ ወንዴ አያይዘው ተናግረዋል።

ጽ/ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መገምገሙ ተቋሙ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ያሉት ተሳታፊዎች በተያዘው በጀት ዓመትም ተቋሙ  ከመማር ማስተማር ፣በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተጠያቂነትና ወጥነት ያለው አሰራር ከመዘርጋት እንዲሁም  ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ከመስራት ጋር በተያያዘ አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው  ጽ/ቤቱ ከተማሪዎች ስነ-ምግባር  እና በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን  የፍሳሽ ማስወገጃ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ተቋሙ በቀጣይም ሊፈታ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ከመድረክ መሰጠቱን ከክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s