በአንድ ማዕከል ለዲያስፖራዎች አገልግሎት መስጠት ተጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አዲስ የዳያስፖራ ማዕከል ዛሬ በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን ማዕከሉ የማህበራዊ ዘርፍ ፣ የኢንቨስትመንት ፣ የኢሚግሬሽንና ሌሎችም አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል የሚሰጥበት ነዉ፡፡
አገልግሎቱም የበአል ቀናትን ጨምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ የሚሰጥ ሲሆን ማዕከሉ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ መሰረት ወደ አገርቤት ለመጡ ዳያስፖራዎች የተለያዩ የመረጃ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነዉ፡፡
በዚህ ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማትም እንኳን ወደ እናት ሀገራችሁ ኢትዮጵያ በሰላም መጣችሁ! እያሉ የዲያስፖራ ማህበረሰቡ አካላት በከተማ አስተዳደሩ በሚከናወኑ የማህበራዊ ዘርፉ ስራዎች ላይ የተደራጀ መረጃ በማግኘት ለማህበራዊ ዘርፉ መጎልበት የድርሻቸዉን እንዲወጡ የመረጃ አገልግሎቱን መስጠት ጀምረዋል፡፡
አካባቢያችንን #እንጠብቅ
ወደ ግንባር #እንዝመት
መከላከያን #እንደግፍ
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!





