የዋንጫ ሽልማት ሳምንት በአብዮት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ በአብዮት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የዋንጫ ሽልማት ሳምንት በመከበር ላይ ነዉ፡፡ የሽልማቱ ዋና አላማ በተማሪዋች መካከል የውድድር መንፈስን በመፍጠር ፣ የመረዳዳት ባህልን የሚያጎለብቱበት እና ለተሻለ ውጤት የሚተጉበት ሌላኛዉ መንገድ አድርጎ እየተጠቀመበት እና የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ ያገዘ መሆኑን ትምህርት ቤቱ ገልጻል።
ትምህርት ቤቱ የሚያከብረው የዋንጫ ሳምንት በወርሀዊ ፈተና ሁሉም ተወዳዳሪ የሚሆንበት እድል ያለው ሲሆን ጓደኞቻቸዉን በማስጠናት እና በወርሃዊ ፈተና 10 ከ10 የደፈኑ ተማሪዎችን ብዛት በየክፍሉ በመቁጠር የላቀ አፈጻጸም ያለዉ ክፍል አሽናፊ የሚሆንበት ነዉ፡፡
በዚህ የዋንጫ ሽልማት ሳምንትም ጓደኞቻቸውን በማስጠናት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ክፍሎች የ1A ፣ የ2B እና የ3A ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ዋንጫዉን ከወተመህ እና ከት/ቤቱ ርዕሰ መምህር በመረከብ በቀጣይም ጓደኞቻቸውን በመረዳት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ቃል ገብተዋል።
ለዚህ የዋንጫ ሽልማት ሳምንት መሳካትም ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ መምህራን ትምህርት ቤቱ ምስጋና አቅርባል።
አካባቢያችንን #እንጠብቅ
ወደ ግንባር #እንዝመት
መከላከያን #እንደግፍ
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


