ቀን 14/4/2014 ዓ.ም

የንባብ ዐውደ ርዕይ በዳግማዊ ሚኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከፈተ፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት ቡድን ባሰናዳው የንባብ ዐውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ደረጄ ገብሬ፣ የተለያዩ መምህራንና የዳግማዊ ሚኒሊክ መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በንባብ የተሟላ ስብዕናው ያለው ትውልድ ለሀገር እድገት መሰረት ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ደረጄ ትውልዱ የንባብ ባህሉን ያሳድግ ዘንድ በት/ቤቶች ግንዛቤ የማስፋት ስራ መሰራቱ ይበል የሚያሰኝ ነውና ሊቀጥል ይገባል ብለው የንባብ ልምዳቸውን ለተማሪዎች አካፍለዋል፡፡

የኪነ-ጥበብ ሀብቶች ልማት፣ የመድረክና ሁነት ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ዳዊት ግርማ በሀገራችን ማንኛውንም እድገት ለማምጣትና ሀገር ለማሻገር አንባቢ ትውልድ መፈጠር አለበት ብለው የእውቀት ምንጭ በሆኑት ትምህርት ቤቶች ላይ የንባብ ባህል ለማሳደግ ታስቦ በተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ በክፍለ ከተማው ለሚገኘው መስከረም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የ52 መፅሀፍት ድጋፍ ይበረከታል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የዝግጅቱ ተሳታፊ ተማሪዎች በማንበብ የተለያዩ እውቀቶችና የህይወት ልምዶችን ማግኘት ስለምንችል የንባብ ባህላችንን ልናሳድግ ይገባል ብለዋል፡፡

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s