በ9ኛው ከተማ አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ሂደት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

 (ግንቦት 14 /2016 ዓ.ም)  በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ የክፍለከተማ ትምህርት እና ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱም የስፖርታዊ ውድርሩን የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ጨምሮ ውድድሩ እስካሁን ያለበትን ሂደት መሰረት አድርጎ ነው የተካሄደው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ እንዳስተዋቁት  ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የ2ኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ስፖርታዊ ውድድር መክፈቻ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የትምህርት ማህበረሰብ በተገኘበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በድምቀት መካሄዱን ገልጸው ቀሪ የስፖርታዊ ውድድሩ መርሃግብርም ሆነ የመዝጊያው ስነ-ስርአት  በስኬትና ከመክፈቻው በተሻለ ደማቅ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚመለከተው ባለድርሻ አካል ከወዲሁ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው  ስፖርታዊ ውድድሩ ከመክፈቻው ቀን ጀምሮ እስካሁን ባለው የውድድር ሂደት በተያዘለት መርሀግብር መሰረት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው የውድድሩን የመዝጊያ ስነስርአት ከ4አመት እድሳት በኃላ ለስፖርታዊ ውድድር ክፍት በሆነው አዲስ አበባ ስቴዲየም በድምቀት ለማካሄድ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ስፖርታዊ ውድድሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት “የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ለሰላም  ፣ለአብሮነትና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል  አትሌቲክስና እግር ኳስን ጨምሮ በ6 የስፖርት አይነቶች እንደሚካሄድ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: – https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com    

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a comment